“ባለፉት ጥቂት ሰዓታት ውስጥ ትልቅ መሻሻል አሳይተናል” ሲሉ ቫንስ ከአሜሪካ–ኢራን ድርድር በፊት ተናገሩ
17:09 21.06.2026 (የተሻሻለ: 17:14 21.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
“ባለፉት ጥቂት ሰዓታት ውስጥ ትልቅ መሻሻል አሳይተናል” ሲሉ ቫንስ ከአሜሪካ–ኢራን ድርድር በፊት ተናገሩ
የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ አሜሪካ፣ ኢራን፣ ፓኪስታን እና ኳታርን ያካተተው የአራቱ ወገኖች ውይይት በስዊዘርላንድ ከመጀመሩ አስቀድሞ ቀጣናዊ ግንኙነቶችን ለመለወጥ ሂደቱ ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ገልጸዋል።
አንኳር የቫንስ ንግግሮች፦
🟠 አሜሪካ "አዲስ ምዕራፍ ለመክፈት" እና "አሮጌ አካሄዷን" መቀየር ትፍልጋለች፣
🟠 የቴክኒክ ውይይቶች እያንዳንዱን አለመግባባት ሙሉ በሙሉ ባይፈቱም፤ ሁለቱንም ወገኖች "በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ቡድን" ያገናኛል፣
🟠 ትራምፕ አሜሪካውያን ተደራዳሪዎች ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ እንዲፈልጉ የፈቀዱ ሲሆን ሁሉን አቀፍ ቀጣናዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ ቁርጠኛ ሆነው እንደቀጠሉ ነው፣
🟠 የትራምፕ አስተዳደር ይህንን ሂደት የመካከለኛው ምስራቅ ግንኙነቶችን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ በዘላቂነት ለመቀየር እንደ መልካም ዕድል ይመለከተዋል፣
🟠 ቫንስ የሊባኖስን የተኩስ አቁም ስምምነት በማስከበር ረገድ መሻሻሎች መታየታቸውን ጠቅሰው፤ እንዲህ ዓይነቶቹ የተኩስ አቁም ስምምነቶች ብዙ ጊዜ "ውጥንቅጥ እንደሚበዛባቸው" ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X