የአሜሪካ–ኢራን ንግግር ተደራዳሪ እና አደራዳሪዎች በስዊዘርላንድ ተሰበሰቡ
16:26 21.06.2026 (የተሻሻለ: 16:34 21.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአሜሪካ–ኢራን ንግግር ተደራዳሪ እና አደራዳሪዎች በስዊዘርላንድ ተሰበሰቡ
ከውይይቱ አስቀድሞ የተሰሙ ጉዳዮች፦
የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሻሪፍ ከአሜሪካ እና ከኢራን ልዑካን ቡድኖች ጋር የተናጠል ስብሰባዎችን አድርገዋል።
የኢራን ልዑካን ቡድን መሪ እና የፓርላማ አፈ-ጉባኤ መሐመድ ባገር ጋሊባፍ ከኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር መሐመድ ቢን አብዱልረህማን አል ታኒ ጋር ተወያይተዋል።
በ60 ቀናት የድርድር ጊዜ ውስጥ የመጨረሻውን ስምምነት ረቂቅ የሚያዘጋጁ የቴክኒክ የሥራ ቡድኖች መቋቋማቸውን ኳታር አስታውቃለች።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ በቡርገንሥቶክ ከስዊዘርላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢኛዚዮ ካሲስ ጋር ውይይት አድርገዋል።
ቴህራን በሊባኖስ የተኩስ አቁም ሳይታወጅ በማዕቀብ መነሳት እና በኒውክሌር ፕሮግራሟ ላይ ድርድር እንደማታደርግ አስታውቃለች።
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ፤ የሀገሪቱ መከላከያ ሠራዊት በደቡብ ሊባኖስ "ለሚሰነዘሩ ጥቃቶች ምላሽ ለመስጠት" ምንም ዓይነት ገደብ እንደሌለበት ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia
© telegram sputnik_ethiopia
© telegram sputnik_ethiopia