“ዘንድሮ በከተማዋ 6 ሚሊዮን ችግኞች ይተከላሉ” - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ሰብስክራይብ

“ዘንድሮ በከተማዋ 6 ሚሊዮን ችግኞች ይተከላሉ” - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ 8ኛውን ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ-ግብር በይፋ አስጀምራለች።

⬆ የችግኝ ተከላውን ያስጀመሩት የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ ባለፉት ሰባት ዓመታት የመዲናዋ የአረንጓዴ ሽፋን ከ2.8% ወደ 24% ማደጉን ገልጸዋል።

“የምንተክለው ተስፋን፣ ልማትን፣ ልምላሜን፣ ጥላን፣ ምግባችንን ብሎም ብልፅግናን ነው። የምንተክለዉ ለዛሬ ጥቅማችን ብቻ ሳይሆን ለትውልድ እዳን ሳይሆን የልምላሜና የብልፅግና ምንዳን ለማውረስ ነው” ብለዋል፡፡

በአረንጓዴ ዐሻራ ማስጀመሪያው ከንቲባዋን ጨምሮ የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎችና ዲፕሎማቶች ዐሻራቸውን አሳርፈዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0