እስራኤል በደቡብ ሊባኖስ በሰነዘረችው ጥቃት 13 ሰዎች ተገደሉ
10:05 21.06.2026 (የተሻሻለ: 10:14 21.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
እስራኤል በደቡብ ሊባኖስ በሰነዘረችው ጥቃት 13 ሰዎች ተገደሉ
ከደቡብ ሊባኖስ ሲዶን አካባቢ የስፑትኒክ ዘጋቢ ያዘጋጀው የቪዲዮ ምሥል ከፍተኛ ውድመት መድረሱን ያሳያል። በጥቃቱ አራት ህንጻዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ፍርስራሽነት የተቀየሩ ሲሆን አንድ የመቃብር ስፍራም ወድሟል።
በጥቃቱ 13 ሰዎች ሲገደሉ 20 ደግሞ መቁሰላቸውን የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። ከሟቾቹ መካከል አምስት ህጻናትና አምስት ሴቶች የሚገኙበት ሲሆን የነፍስ አድን ቡድኖች በፍርስራሹ ውስጥ ፍለጋ ማካሄዳቸውን አሁንም ቀጥለዋል።
እስራኤል ድርድሮች እየተካሄዱ ባሉበት ወቅት ሊባኖስ ላይ የምታካሂደው ጥቃት፤ ለአሜሪካ እና ኢራን ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ዋነኛ እንቅፋት ሆኖ ቀጥሏል። የትኛውም ዓይነት ጥሰት የአጸፋ እርምጃ እንደሚያስከትል ያስጠነቀቀችው ኢራን፤ ከወዲሁ የሆርሙዝ ወሽመጥን በድጋሚ ዘግታለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia