ሞሪሸስ በሕንድ ውቅያኖስ ለሩሲያ መርከበኞች መታሰቢያ ሐውልት አቆመች

ሰብስክራይብ

ሞሪሸስ በሕንድ ውቅያኖስ ለሩሲያ መርከበኞች መታሰቢያ ሐውልት አቆመች

​ “የሩሲያ ባንዲራ በሕንድ ውቅያኖስ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የመታየቱ ምልክት” የሆነ አዲስ መታሰቢያ ሐውልት ተተክሏል።

​መርከበኞቹ በ1857 እ.ኤ.አ “ኦሊቩትሳ” በተባለች የጦር መርከብ አየተጓዙ በነበረበት ወቅት በመርከቧ ላይ በተከሰተ የበሽታ ወረርሽኝ ምክንያት መርከቧ በደሴቲቱ ላይ ያልታቀደ ማቆሚያ ለማድረግ ተገድዳ ነበር። የሕክምና ክትትል ቢደረግላቸውም ስድስት የመርከቧ አባላት ሕይወታቸው አልፎ በደሴቲቱ ላይ ተቀብረዋል።

በሞሪሸስ የሩሲያ አምባሳደር ኢራዳ ዜይናሎቫ ታሪኩን “የማይታመን ድፍረት እና የመንፈስ ጥንካሬ” ማሳያ በማለት ገልጸውታል።

​ በሩሲያ ኤምባሲ ውስጥ አነስተኛ የመታሰቢያ ሙዚየም እየተቋቋመ መሆኑን የጠቀሱት አምባሳደሯ፤ ሙዚየሙ ለ “ኦሊቩትሳ” መርከብ ብቻ ሳይሆን በሕንድ እና በፓስፊክ ውቅያኖሶች ላይ የነበረውን ሰፊ የሩሲያ የባሕር ጉዞ ታሪክ ጭምር የሚዘክር መሆኑን አክለው ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0