አዲሱ የቱሪዝም ፖሊሲ መስህቦችን እና መዳረሻዎችን ለማበራከት ሰፊ ዕድል ይፈጥራል - የቱሪዝም ሚኒስቴር

ሰብስክራይብ

አዲሱ የቱሪዝም ፖሊሲ መስህቦችን እና መዳረሻዎችን ለማበራከት ሰፊ ዕድል ይፈጥራል - የቱሪዝም ሚኒስቴር

በኢትዮጵያ የቱሪስት አስጎብኝዎች “ኢትዮጵያ በቱሪስት አስጎብኝዎች ዓይን” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውን 4ኛው የፎቶግራፍ ዐውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ሙዚየም በይፋ ተከፍቷል።

የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ ከወራት በፊት በሚኒስትሮች ምክር ቤት የጸደቀው አዲሱ የቱሪዝም ፖሊሲ ነባር ባህላዊ እና ታሪካዊ ቅርሶችን ይበልጥ ከማስተዋወቅ ባለፈ፥ የዘርፉን ተዋናዮች አቅም ለማጎልበትና የቱሪዝም ገቢን ለማሳደግ ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግም ጠቁመዋል።

በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን ውስጥም ቢሆን የአንድን አገር የጉብኝት መዳረሻዎች በማስተዋወቅ ረገድ የፎቶግራፍ ሚና ዘመን ተሻጋሪ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታው፤ የዘርፉ ባለሙያዎች ጊዜው ያፈራቸውን የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች በስፋት እንዲጠቀሙ አሳስበዋል።

በ19 የቱሪስት አስጎብኝዎች የተነሱና በውድድር የተመረጡ 72 ድንቅ ፎቶግራፎች ለእይታ መቅረባቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል፡፡

ዐውደ ርዕዩ ዛሬን ጨምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ለሕዝብ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ተገልጿል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0