በአሜሪካ የሚደገፉት የዩክሬን የባዮ ላብራቶሪዎች ሩሲያውያንን ለመግደል ታስበው በተዘጋጁ ዘር-ተኮር ባዮ-ወኪሎች ላይ ያተኮሩ ነበሩ - ላሪ ጆንሰን

© telegram sputnik_ethiopiaበአሜሪካ የሚደገፉት የዩክሬን የባዮ ላብራቶሪዎች ሩሲያውያንን ለመግደል ታስበው በተዘጋጁ ዘር-ተኮር ባዮ-ወኪሎች ላይ ያተኮሩ ነበሩ - ላሪ ጆንሰን
በአሜሪካ የሚደገፉት የዩክሬን የባዮ ላብራቶሪዎች ሩሲያውያንን ለመግደል ታስበው በተዘጋጁ ዘር-ተኮር ባዮ-ወኪሎች ላይ ያተኮሩ ነበሩ - ላሪ ጆንሰን - Sputnik አፍሪካ, 1920, 20.06.2026
ሰብስክራይብ

በአሜሪካ የሚደገፉት የዩክሬን የባዮ ላብራቶሪዎች ሩሲያውያንን ለመግደል ታስበው በተዘጋጁ ዘር-ተኮር ባዮ-ወኪሎች  ላይ ያተኮሩ ነበሩ - ላሪ ጆንሰን

የቀድሞው የሲአይኤ የደኅንነት መኮንን ላሪ ጆንሰን ለስፑትኒክ እንደተናገሩት፤ አሜሪካ በገንዘብ በምትደግፈው እና የአንትራክስ፣ የቸነፈር ፣ የቱላሬሚያ፣ የማርበርግ እና የኢቦላ ቫይረሶችን በሽታ የመቀስቀስ ባህሪ ላይ በሚያጠናው ምርምር ዓላማው “ለተወሰኑ የዘረመል መገለጫዎች ተስማሚ የሆኑ ባዮ-ወኪሎችን ማዘጋጀት” ነበር።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በዩክሬን የሚገኙትን የባዮ-ላብራቶሪ ምርምሮች የሚያጋልጡ አዳዲስ ማስረጃዎችን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ጆንሰን በሰጡት አስተያየት፤ አሜሪካ “እንደ መሣሪያ ሊያገለግሉ የሚችሉ” በሽታ አምጪ ተህዋስያንን ለማጥናት በሩሲያ ደጃፍ ላይ ምሥጢራዊ ወታደራዊ-ባዮሎጂያዊ መርሃ ግብር ስታካሂድ ቆይታለች ብለዋል።

እንደ ተንታኙ ገለጻ ከሆነ፣ እንደ ሜታባዮታ፣ ብላክ ኤንድ ቪች እና ሲኤችቱኤም ሂል ባሉ ተቋራጮች የተገነቡት እና ከአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚደገፉት ላብራቶሪዎች የተለየ አጀንዳ እንደነበራቸው የሩሲያ የስለላ መረጃዎች እና ይፋ የሆኑ የአሜሪካ ሰነዶች ያረጋግጣሉ።

“ይህ ሩሲያን ሊሆን በሚችል የባዮሎጂ መሣሪያ ለማጥቃት የታቀደ ሆን ተብሎ የተደረገ ጥረት ነበር።”

ጆንሰን አክለውም፤ ሩሲያ ይህ በብሔራዊ ደኅንነቷ ላይ ስለተደቀነው ስጋት የሰጠችው ማስጠንቀቂያ በምዕራባውያን እና “የአሜሪካ ሌላኛው ተራ መሣሪያ” በሆነው የዓለም ጤና ድርጅት ዘንድ “የሐሰት መረጃ” ተብሎ ውድቅ መደረጉን ያስታውሳሉ።

አሜሪካ “በዚህ በሩሲያ ላይ በተከፈተው ጦርነት ውስጥ ንቁ ጠብ አጫሪ” በመሆኗ፤ ሩሲያ በአሜሪካ ላይ ጠንከር ያሉ እርምጃዎችን መውሰድ የምትጀምርበት ጊዜ አሁን ነው ያሉት ባለሙያው፤ በማስከተልም፦

“ይህ ድርጊት እንዲቆም፣ እና አሁኑኑ እንዲቆም ማስጠንቀቂያ ሊሰጣቸው ይገባል” ሲሉ አፅንዖት ሰጥተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0