አሜሪካ እና ኳታር በታገደው የኢራን 6 ቢሊዮን ዶላር ፈንድ ለሰብዓዊ ቁሳቁሶች ግዢ የሚውልበትን መንገድ ለመክፈት እየሰሩ ነው - ሪፖርት

© telegram sputnik_ethiopiaአሜሪካ እና ኳታር በታገደው የኢራን 6 ቢሊዮን ዶላር ፈንድ ለሰብዓዊ ቁሳቁሶች ግዢ የሚውልበትን መንገድ ለመክፈት እየሰሩ ነው - ሪፖርት
አሜሪካ እና ኳታር በታገደው የኢራን 6 ቢሊዮን ዶላር ፈንድ ለሰብዓዊ ቁሳቁሶች ግዢ የሚውልበትን መንገድ ለመክፈት እየሰሩ ነው - ሪፖርት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 20.06.2026
ሰብስክራይብ

አሜሪካ እና ኳታር በታገደው የኢራን 6 ቢሊዮን ዶላር ፈንድ ለሰብዓዊ ቁሳቁሶች ግዢ የሚውልበትን መንገድ ለመክፈት እየሰሩ ነው - ሪፖርት

የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ምንጮችን ጠቅሰው እንደዘገቡት፤ አገራቱ ኢራን በታገደባት 100 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ከሚገመተው ሀብት ውስጥ በኳታር ከሚገኘው 6 ቢሊዮን ዶላር ጀምሮ በከፊል እንድታገኝ የሚያስችል ዕቅድ እያዘጋጁ ነው።

ኳታር የኢራን ማዕከላዊ ባንክ ፈንዱን በመጠቀም ምግብ፣ መድኃኒት እና ሌሎች ሰብዓዊ ቁሳቁሶችን መግዛት የሚያስችለውን ሥርዓት እንደምትመራ የተነገረ ሲሆን፤ ገንዘቡም ከታገደው የነዳጅ ሽያጭ የሚገኝ ነው።

ይህ ጥረት የተጀመረው ጦርነቱን ለማቆም የታለመውና በቅርቡ የተፈረመውን የመግባቢያ ስምምነት ተከትሎ የመጣ ነው።

በአሜሪካ ማዕቀብ ምክንያት የኢራን የፋይናንስ ሀብቶች በመላው ዓለም እንደታገዱ መቆየታቸው ይታወቃል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0