ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ታግዛ የአፍሪካ ሁለተኛዋ ከፍተኛ የአቮካዶ ላኪ ሆነች - ግብርና ሚኒስቴር

© telegram sputnik_ethiopiaኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ታግዛ የአፍሪካ ሁለተኛዋ ከፍተኛ የአቮካዶ ላኪ ሆነች - ግብርና ሚኒስቴር
ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ታግዛ የአፍሪካ ሁለተኛዋ ከፍተኛ የአቮካዶ ላኪ ሆነች - ግብርና ሚኒስቴር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 20.06.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ታግዛ የአፍሪካ ሁለተኛዋ ከፍተኛ የአቮካዶ ላኪ ሆነች - ግብርና ሚኒስቴር

የግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ፣ ላለፉት ሰባት ዓመታት በአገር አቀፍ ደረጃ 48 ቢሊዮን ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥ 60 በመቶ የሚሆኑት ለምግብ ዋስትና እና ገቢ ማስገኛ (በተለይም እንደ አቮካዶ ያሉ ፍራፍሬዎች) የዋሉ ሲሆን 35 በመቶው ደግሞ ለከተማ ውበት የተተከሉ መሆናቸውን ገልፀዋል።

አገሪቱ በያዘችው ብሔራዊ የአቮካዶ ልማት መርሃ ግብር አማካኝነት በአሁኑ ወቅት በአኅጉሪቱ ያላትን የሁለተኛ ደረጃ ቦታ በማሻሻል በቀጣዮቹ ዓመታት በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም የአቮካዶ ላኪ አገር ለመሆን እየሠራች እንደምትገኝ ሚኒስትሩ መጠቆማቸው ተዘግቧል።

የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር አካል የሆኑት የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች የተፈጥሮ ሀብትን በማደስ ለአጠቃላይ የሰብል ምርት ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ማበርከታቸውም ተገልጿል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0