- Sputnik አፍሪካ, 1920
Continental Drift
በአፍሪካ ቅርፅ እየቀየሩ ያሉትን እንደዚሁም የደቡባዊውን ዓለም ክፍል ሚና በአዲስ መልክ እየገለጹ ያሉትን ስር ነቀል ለውጦች የሚቃኝ ፕሮግራም ነው። ትዕይንቱ ፖሊሲዎች፣ ገበያዎች እና ፈጠራዎች ከዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር እንዴት እንደሚገናኙ በመመርመር በእውነታ ላይ የተመሰረቱ ግንዛቤዎችን እና ትክክለኛ የአፍሪካ አመለካከቶችን ያቀርባል።

የህዳሴው ግድብ በቡድን 7 አባል አገራት ስብሰባ፡- የትራምፕ ቃል እና የኢትዮጵያ ሉዓላዊ መብት

የህዳሴው ግድብ በቡድን 7 አባል አገራት ስብሰባ፡- የትራምፕ ቃል እና የኢትዮጵያ ሉዓላዊ መብት
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ወሳኝ ከመሆኑ ባለፈ፣ የሉዓላዊነት እና የቀጣናዊ ዲፕሎማሲ ተምሳሌት ሆኗል። በቅርቡ ደግሞ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቡድን 7 አባል ሀገራት ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የግድቡ ግንባታ በግብፅ ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን በመጥቀስ አሜሪካ በድጋሚ የመደራደር ፍላጎት እንዳላት ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡
"ትራምፕ በኢትዮጵያ እና በግብፅ መካከል ለመደራደር ሞክረው ነበር። በመጨረሻም ኢትዮጵያ ሀብቷን የመጠቀም ሉዓላዊ መብቷን የሚገፍ እና ተቀባይነት የሌለው ስምምነት ተረቅቆ ነበር፤ ይሄ ስምምነት በኋላ በባይደን አስተዳደር እንዲነሳ ተደርጓል። አሁን ደግሞ ለፕሬዝዳንት ሲሲ ይህን ሂደት እንደሚጀምሩ ቃል እየገቡ ነው፤ ምንም የተለየ አዲስ ነገር ይዘው እንደሚመጡ አልጠብቅም።" ሲሉ ፈቃአህመድ ነጋሽ፣ የድንበር ተሻጋሪ የውሃ አስተዳደር እና የሃይድሮ-ፖለቲካ አማካሪ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የህዳሴ ግድብን ዲፕሎማሲያዊ እና ህጋዊ ውስብስብነት እንዲሁም የኢትዮጵያን አዳዲስ የኦዲት ማሻሻያዎች በሁለት አቅጣጫዎች እንፈትሻለን። ለዚህም የድንበር ተሻጋሪ የውሃ አስተዳደር እና የሃይድሮ-ፖለቲካ አማካሪ ፈቃአህመድ ነጋሽ እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የገንዘብ ዘርፍ ሀላፊ ተመስገን ጌታዬ ጋር ቆይታ አድርገናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripods Pocket CastsPodcast AddictCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0