የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ዋና ዓቃቤ ሕግ ካሪም ኻን በፈጸሙት የወሲብ ጥቃት ክስ ከኃላፊነታቸው ሊነሱ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ድምፅ ሊሰጥባቸው ነው - መገናኛ ብዙኃን

© telegram sputnik_ethiopiaየዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ዋና ዓቃቤ ሕግ ካሪም ኻን በፈጸሙት የወሲብ ጥቃት ክስ ከኃላፊነታቸው ሊነሱ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ድምፅ ሊሰጥባቸው ነው - መገናኛ ብዙኃን
የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ዋና ዓቃቤ ሕግ ካሪም ኻን በፈጸሙት የወሲብ ጥቃት ክስ ከኃላፊነታቸው ሊነሱ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ድምፅ ሊሰጥባቸው ነው - መገናኛ ብዙኃን - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.06.2026
ሰብስክራይብ

የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ዋና ዓቃቤ ሕግ ካሪም ኻን በፈጸሙት የወሲብ ጥቃት ክስ ከኃላፊነታቸው ሊነሱ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ድምፅ ሊሰጥባቸው ነው - መገናኛ ብዙኃን

ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ዋና ዓቃቤ ሕጉን ካሪም ኻንን በዘላቂነት ከኃላፊነታቸው ለማንሳት ውሳኔ ለመስጠት በመጪው ሐምሌ 17 ቀን ልዩ ስብሰባ ሊያካሂድ መሆኑን የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች አመላክተዋል።

የፍርድ ቤቱ የቁጥጥር አካል በከባድ የሥነ-ምግባር ጉድለት ላይ በቂ ማስረጃ ማግኘቱ የተነገረ ሲሆን፤ ካሪም ኻን ግን የቀረበባቸውን ክስ ሁሉ በጽኑ አስተባብለዋል። የሕግ ባለሙያዎቻቸውም የቀረበውን ሪፖርት “እጅግ ጉድለት ያለበት” እና “ሕገ-ወጥ” ሲሉ ጠርተውታል።

በካሪም ኻን ላይ የቀረቡት የመጀመሪያዎቹ ክሶች ይፋ የሆኑት እ.ኤ.አ. በ2024 ሲሆን፤ ይህም ከጋዛ ግጭት ጋር ተያይዞ በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ እንዲወጣ በጠየቁ ሳምንታት ውስጥ ነበር። ካሪም ኻን ከሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ከሥራ ታግደው ይገኛሉ

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0