በአዲስ አበባ የነዋሪነት እና የሲቪል ምዝገባ አገልግሎቶችን በበይነ መረብ መስጠት የሚያስችል ዲጂታል ሥርዓት በይፋ ጀመረ

ሰብስክራይብ

🪪 በአዲስ አበባ የነዋሪነት እና የሲቪል ምዝገባ አገልግሎቶችን በበይነ መረብ መስጠት የሚያስችል ዲጂታል ሥርዓት በይፋ ጀመረ

የከተማ አስተዳደሩ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ፣ ነዋሪዎች ያሉበት ቦታ ሆነው አገልግሎት ማግኘት የሚችሉበትን ዘመናዊ የኦንላይን ሥርዓት ሥራ ላይ ማዋሉን አስታውቋል።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዮሴፍ ንጉሤ ቴክኖሎጂው ቀልጣፋና ከብልሹ አሠራር የጸዳ አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም የሐሰተኛ ሰነዶች ዝውውርን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ትልቅ ሚና እንዳለው አብራርተዋል።

ተገልጋዮች በተዘጋጀው ድረ-ገጽ ላይ በመግባት አገልግሎቱን ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፤ በመረጃዎቻቸው ላይ ስህተት ቢፈጠር እንኳ ባሉበት ሆነው ራሳቸው ማስተካከል የሚችሉበት አሠራር መዘርጋቱ ተጠቁሟል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0