ለኪዬቭ በዐውደ-ግንባር ያለው ሁኔታ እየከፋ እንደመሄዱ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታደርገውን ጥቃት ትቀጥላለች - ክሬምሊን
17:17 19.06.2026 (የተሻሻለ: 17:24 19.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ለኪዬቭ በዐውደ-ግንባር ያለው ሁኔታ እየከፋ እንደመሄዱ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታደርገውን ጥቃት ትቀጥላለች - ክሬምሊን
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ፤ ሰሞኑን የተፈፀሙ ጥቃቶች ውጤታማ መሆናቸውን በመግለጽ ሩሲያ በዩክሬን የምታካሂደውን ወታደራዊ ዘመቻ እንደምትቀጥልና በጦር ግንባር ላይ ያለው የኪዬቭ አቋም በየጊዜው እየተዳከመ መምጣቱን ተናግረዋል።
ሌሎች የቃል አቀባዩ መግለጫዎች፦
ሰሞኑን በሩሲያ የተሰነዘሩት ጥቃቶች ውጤቶች አስደናቂ ነበሩ፡፡
አውሮፓ የዩክሬንን ግጭት ጨምሮ አሁን ያለውን ተጨባጭ የምድር ላይ እውነት በሚገባ ልትረዳው ይገባል፡፡
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሩሲያ ከአውሮፓ ጋር ለሚደረጉ ግንኙነቶች ምንጊዜም ክፍት መሆኗን በተደጋጋሚ ገልጸዋል፡፡
በሩሲያ እና በአውሮፓ መካከል ያለው የውይይት አስፈላጊነት በተፈጥሯዊ አስተውሎት የሚመራ ነው፡፡
ሩሲያ የታላቁ የአርበኝነት ጦርነት የተጀመረበትን መታሰቢያ የምታስብ ሲሆን፤ በወቅቱ ለሞቱትም ሐዘኗን ትገልጻለች፡፡
በሰኔ 15 ቀን በሚከበረው የማስታወሻ እና የሐዘን ቀን ላይ ፕሬዝዳንት ፑቲን በሞስኮ በሚገኘው ባልታወቀው ወታደር መቃብር ላይ የአበባ ጉንጉን ያኖራሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X