ለጋሾች የኢቦላ ወረርሽኝ ‘እጅግ አሳሳቢ ምዕራፍ’ ላይ መድረሱን ተከትሎ የ910 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገቡ - የአፍሪካ ሲዲሲ

© telegram sputnik_ethiopiaለጋሾች የኢቦላ ወረርሽኝ ‘እጅግ አሳሳቢ ምዕራፍ’ ላይ መድረሱን ተከትሎ የ910 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገቡ - የአፍሪካ ሲዲሲ
ለጋሾች የኢቦላ ወረርሽኝ ‘እጅግ አሳሳቢ ምዕራፍ’ ላይ መድረሱን ተከትሎ የ910 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገቡ - የአፍሪካ ሲዲሲ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.06.2026
ሰብስክራይብ

ለጋሾች የኢቦላ ወረርሽኝ ‘እጅግ አሳሳቢ ምዕራፍ’ ላይ መድረሱን ተከትሎ የ910 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገቡ - የአፍሪካ ሲዲሲ

ከአፍሪካ ሕብረት አባል አገራት የተገኘውን 80 ሚሊዮን ዶላር ጨምሮ፣ የተሰበሰበው ገንዘብ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በኡጋንዳ እየተደረገ ያለውን የኢቦላ መከላከል ሥራ ለመደገፍ የሚውል መሆኑን የአፍሪካ የበሽታ መከላከል እና ቁጥጥር ማዕከል (የአፍሪካ ሲዲሲ) በበይነ መረብ ከተካሄደው የፕሬዝዳንቶች ስብሰባ በኋላ አስታውቋል።

አኅጉራዊው ተቋም እንዳመለከተው እስከ ሰኔ 8 ቀን ድረስ በወረርሽኙ የተያዙ 827 የተረጋገጡኬዞች እና 194 ሞት ተመዝግበዋል፡፡

ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ፦ 808 በበሽታው ሲያዙ፣ 192 ሞተዋል፡፡

ኡጋንዳ፦ 19 በበሽታው ተይዘዋል፤ 2  ሰዎች ሞተዋል፡፡

የስብሰባው ዋና ዋና ውጤቶች፦

🟠 ባለ 6 ወራት የ518 ሚሊዮን ዶላር የጋራ ምላሽ ዕቅድ ፀድቋል፡፡

🟠 መሪዎች የበሽታው ተሸካሚዎችን የመከታተል፣ የሕክምና እና የማኅበረሰብ ተሳትፎ ሥራዎችን ለማቀጣጠል የሰባት ቀናት የተጠናከረ የዘመቻ ሥራ እንዲጀመር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

🟠 ለቡንዲቡግዮ የቫይረስ ዝርያ እስካሁን የጸደቀ ክትባትም ሆነ መድኃኒት የለም፡፡

🟠 አጠቃላይ የጉዞ እገዳዎችን በሕብረተሰብ ጤና ሳይንሳዊ መረጃዎች ተደገፉ አለመሆናቸው ተገልጿል።

የአፍሪካ ሲዲሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዣን ካሴያ፣ የተደረገውን የገንዘብ ቃል ኪዳን በደስታ በመቀበል፤ “አፍሪካ ከተደጋጋሚ የአደጋ ጊዜ ጥሪዎች ወጥታ፣ አስቀድሞ ወደሚታወቅ የቅድመ ዝግጅት ኢንቨስትመንት መሸጋገር አለባት” ብለዋል።

በተጨማሪም ስብሰባው ለወረርሽኝ ቅድመ ዝግጅት እና ለአገር ውስጥ (ለቀጣናው) ምርት ማሳደጊያ የሚሆን፤ ከአፍሪካ አገራት እና ከግል ዘርፉ በየዓመቱ የሚሰበሰብ የ100 ሚሊዮን ዶላር የበጎ ፈቃድ ፋይናንስን አጽድቋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0