https://amh.sputniknews.africa/20260619/4362942.html
‘ይህ የውሳኔ ሐሳብ መድረሻ ሳይሆን የ‘ጉዞ’ መጀመሪያ ነው’፦ የአፍሪካ መሪዎች ስለ ታሪካዊ ፍትሕ እና ካሳ ክፍያ
‘ይህ የውሳኔ ሐሳብ መድረሻ ሳይሆን የ‘ጉዞ’ መጀመሪያ ነው’፦ የአፍሪካ መሪዎች ስለ ታሪካዊ ፍትሕ እና ካሳ ክፍያ
Sputnik አፍሪካ
‘ይህ የውሳኔ ሐሳብ መድረሻ ሳይሆን የ‘ጉዞ’ መጀመሪያ ነው’፦ የአፍሪካ መሪዎች ስለ ታሪካዊ ፍትሕ እና ካሳ ክፍያ በጋና አክራ በተካሄደው “የሚቀጥሉት እርምጃዎች” ዓለም አቀፍ የታሪካዊ ፍትሕ እና ካሳ ክፍያ ጉባኤ ላይ፤ የአፍሪካ ፕሬዚዳንቶች... 19.06.2026, Sputnik አፍሪካ
2026-06-19T09:55+0300
2026-06-19T09:55+0300
2026-06-19T10:04+0300
sputnik africa
telegram sputnik_ethiopia
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/06/13/4362789_5:0:1285:720_1920x0_80_0_0_6a20898304c18fc07f976375147fc85a.jpg
‘ይህ የውሳኔ ሐሳብ መድረሻ ሳይሆን የ‘ጉዞ’ መጀመሪያ ነው’፦ የአፍሪካ መሪዎች ስለ ታሪካዊ ፍትሕ እና ካሳ ክፍያ በጋና አክራ በተካሄደው “የሚቀጥሉት እርምጃዎች” ዓለም አቀፍ የታሪካዊ ፍትሕ እና ካሳ ክፍያ ጉባኤ ላይ፤ የአፍሪካ ፕሬዚዳንቶች የአትላንቲክ ውቅያኖስ የባሪያ ንግድን በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል አድርጎ የደነገገውን የቅርብ ጊዜውን የተባበሩት መንግሥታት የውሳኔ ሐሳብ ወደ ተግባር ለመለወጥ ጥሪ ማቅረባቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ዘግቧል። የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ፦“ይህ የውሳኔ ሐሳብ ተራ ምሳሌያዊ ምልክት ሆኖ መቅረት የለበትም። በማንነት እና በወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ የተመሠረተ አዲስ ጎዳና መክፈት አለበት። ፍትሕ የጋራ ኃላፊነት ነው” ብለዋል። የካሳ ክፍያ ታሪካዊ እውነትን፣ የክብር መመለስን እና የዘረኝነትን ትግል የሚያካትት መሆኑን አጽንኦት በመስጠት፤ ወጣቶችን፣ ከያንያንን (አርቲስቶችን) እና ሲቪል ማኅበረሰቡን ያሳተፉ ተጨባጭ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጥሪ አቅርበዋል። የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ቦአካይ፦ይህ ጉባኤ የውሳኔ ሐሳቡ ለእውነት፣ ለፍትሕ፣ ለማገገምና ለተቋማዊ ጥገና ማዕቀፍ መሆኑን ለማረጋገጥ ያለመ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ትርጉም ያለው የካሳ ክፍያ ከገንዘብ ማዕቀፍ ባለፈ ታሪካዊ እውነትን፣ የማንነት መመለስን እና ተቋማዊ ጥንካሬን ማካተት እንዳለበት አሳስበዋል። የናሚቢያ ፕሬዚዳንት ኔቱምቦ ናንዲ-ንዳይትዋ፦የውሳኔ ሐሳቡን እንደ አንድ ትልቅ ምዕራፍ የገለጹት ቢሆንም፤ መድረሻ ሳይሆን ወደ እውነት፣ ዕውቅና መስጠት፣ ማገገም እና ፍትሕ የሚመራ የጉዞ መጀመሪያ መሆኑን ጠቅሰዋል። እውነተኛ እርቅ የሚጀምረው ሰዎች የራሳቸውን ታሪክ እንዲናገሩ ሲፈቀድላቸው እና ታሪካቸውም በሐቀኝነት ተቀባይነት ሲያገኝ ነው ሲሉ አክለዋል። የጋና ፕሬዚዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ፦“እዚህ የተሰበሰብነው ስለ ቀደመው ታሪክ ለመወያየት ብቻ ሳይሆን፤ በሕዝባችን ላይ እስካሁን ከተፈጸሙት ታላላቅ ወንጀሎች መካከል አንዱ ለሆነው ድርጊት የሰው ልጅ ምን ዓይነት ምላሽ እንደሚሰጥ ለመወሰን ጭምር ነው” ብለዋል። ይህ ትውልድ መርከቦቹን ባይገነባም ወይም የእርሻ ቦታዎቹን ባያስተዳድርም “እያንዳንዱ ትውልድ ከባለፈው ታሪክ ኃላፊነቶችን ይወርሳል” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2026
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
‘ይህ የውሳኔ ሐሳብ መድረሻ ሳይሆን የ‘ጉዞ’ መጀመሪያ ነው’፦ የአፍሪካ መሪዎች ስለ ታሪካዊ ፍትሕ እና ካሳ ክፍያ
Sputnik አፍሪካ
‘ይህ የውሳኔ ሐሳብ መድረሻ ሳይሆን የ‘ጉዞ’ መጀመሪያ ነው’፦ የአፍሪካ መሪዎች ስለ ታሪካዊ ፍትሕ እና ካሳ ክፍያ
2026-06-19T09:55+0300
true
PT1S
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/06/13/4362789_165:0:1125:720_1920x0_80_0_0_1b32a96ba4b24610a42ecb93f77ab9e8.jpgSputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
‘ይህ የውሳኔ ሐሳብ መድረሻ ሳይሆን የ‘ጉዞ’ መጀመሪያ ነው’፦ የአፍሪካ መሪዎች ስለ ታሪካዊ ፍትሕ እና ካሳ ክፍያ
09:55 19.06.2026 (የተሻሻለ: 10:04 19.06.2026) ‘ይህ የውሳኔ ሐሳብ መድረሻ ሳይሆን የ‘ጉዞ’ መጀመሪያ ነው’፦ የአፍሪካ መሪዎች ስለ ታሪካዊ ፍትሕ እና ካሳ ክፍያ
በጋና አክራ በተካሄደው “የሚቀጥሉት እርምጃዎች” ዓለም አቀፍ የታሪካዊ ፍትሕ እና ካሳ ክፍያ ጉባኤ ላይ፤ የአፍሪካ ፕሬዚዳንቶች የአትላንቲክ ውቅያኖስ የባሪያ ንግድን በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል አድርጎ የደነገገውን የቅርብ ጊዜውን የተባበሩት መንግሥታት የውሳኔ ሐሳብ ወደ ተግባር ለመለወጥ ጥሪ ማቅረባቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ዘግቧል።
የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ፦
“ይህ የውሳኔ ሐሳብ ተራ ምሳሌያዊ ምልክት ሆኖ መቅረት የለበትም። በማንነት እና በወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ የተመሠረተ አዲስ ጎዳና መክፈት አለበት። ፍትሕ የጋራ ኃላፊነት ነው” ብለዋል። የካሳ ክፍያ ታሪካዊ እውነትን፣ የክብር መመለስን እና የዘረኝነትን ትግል የሚያካትት መሆኑን አጽንኦት በመስጠት፤ ወጣቶችን፣ ከያንያንን (አርቲስቶችን) እና ሲቪል ማኅበረሰቡን ያሳተፉ ተጨባጭ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጥሪ አቅርበዋል።
የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ቦአካይ፦
ይህ ጉባኤ የውሳኔ ሐሳቡ ለእውነት፣ ለፍትሕ፣ ለማገገምና ለተቋማዊ ጥገና ማዕቀፍ መሆኑን ለማረጋገጥ ያለመ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ትርጉም ያለው የካሳ ክፍያ ከገንዘብ ማዕቀፍ ባለፈ ታሪካዊ እውነትን፣ የማንነት መመለስን እና ተቋማዊ ጥንካሬን ማካተት እንዳለበት አሳስበዋል።
የናሚቢያ ፕሬዚዳንት ኔቱምቦ ናንዲ-ንዳይትዋ፦
የውሳኔ ሐሳቡን እንደ አንድ ትልቅ ምዕራፍ የገለጹት ቢሆንም፤ መድረሻ ሳይሆን ወደ እውነት፣ ዕውቅና መስጠት፣ ማገገም እና ፍትሕ የሚመራ የጉዞ መጀመሪያ መሆኑን ጠቅሰዋል። እውነተኛ እርቅ የሚጀምረው ሰዎች የራሳቸውን ታሪክ እንዲናገሩ ሲፈቀድላቸው እና ታሪካቸውም በሐቀኝነት ተቀባይነት ሲያገኝ ነው ሲሉ አክለዋል።
የጋና ፕሬዚዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ፦
“እዚህ የተሰበሰብነው ስለ ቀደመው ታሪክ ለመወያየት ብቻ ሳይሆን፤ በሕዝባችን ላይ እስካሁን ከተፈጸሙት ታላላቅ ወንጀሎች መካከል አንዱ ለሆነው ድርጊት የሰው ልጅ ምን ዓይነት ምላሽ እንደሚሰጥ ለመወሰን ጭምር ነው” ብለዋል። ይህ ትውልድ መርከቦቹን ባይገነባም ወይም የእርሻ ቦታዎቹን ባያስተዳድርም “እያንዳንዱ ትውልድ ከባለፈው ታሪክ ኃላፊነቶችን ይወርሳል” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X