የአፍሪካ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን ለመጠቀም የተሳሰረ የጋራ የኃይል አውታር መገንባት አለባቸው - የደቡብ አፍሪካ ሚኒስትር

ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን ለመጠቀም የተሳሰረ የጋራ የኃይል አውታር መገንባት አለባቸው - የደቡብ አፍሪካ ሚኒስትር

አንድ ወጥ የኤሌክትሪክ ገበያ፣ በመላ አኅጉሪቱ የኃይል እጥረት ለሚያጋጥማቸው ሀገራት የኃይል አቅርቦትን ለማድረስ ያስችላል ሲሉ የኤሌክትሪክና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ክጎሴንትሾ ራሞክጎፓ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

"አብዛኛው የአፍሪካ አኅጉር የማዕድን ቁፋሮ ላይ ተሰማርቷል። ነገር ግን በኤሌክትሪክ እጥረት ምክንያት ምርቱን እሴት ጨምረው ማውጣት አይችሉም፤ ምክንያቱም አሁን ባለው ሁኔታ በቤንዚን ላይ ለመደገፍ ስለሚገደዱ ተወዳዳሪ መሆን አልቻሉም" ሲሉ ሚኒስትሩ ከአፍሪካ ኢነርጂ ፎረም ጎን ለጎን በሰጡት አስተያየት ጠቁመዋል።

ከኃይል ትስስር በተጨማሪ በፎረሙ ላይ "ሚሽን 300" ተነሳሽነት መወያያ እንደነበር የገለጹት ሚኒስትሩ፣ አፍሪካ የዚህን ተነሳሽነት ግብ እንደምታሳካ ያላቸውን ዕምነት አክለው ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0