ትራምፕ የሕዳሴ ግድብ ድርድርን በተመለከተ “የተለየ ዕቅድ ይዘው እንደማይመጡ እርግጠኛ ነኝ” – ኢትዮጵያዊ ባለሙያ
08:03 19.06.2026 (የተሻሻለ: 08:34 19.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ትራምፕ የሕዳሴ ግድብ ድርድርን በተመለከተ “የተለየ ዕቅድ ይዘው እንደማይመጡ እርግጠኛ ነኝ” – ኢትዮጵያዊ ባለሙያ
የድንበር ተሻጋሪ ውኃዎች እና የሃይድሮ-ፖለቲካ አማካሪው ፈቅአህመድ ነጋሽ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከግብፁ አቻቸው አብደል ፈታህ ኤል-ሲሲ ጋር ከተገናኙ በኋላ በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ አዲስ ድርድር ለማስጀመር ማቀዳቸውን መግለፃቸውን አስመልክቶ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ በፕሬዝዳንቱ በኩል አዲስ የሀሳብ ለውጥ ይኖራል ተብሎ እንደማይጠበቅ ተናግረዋል፡፡
“እሳቸው (ትራምፕ) የተለየ ዕቅድ (ማደራደሪያ) ይዘው ይመጣሉ ብዬ አላምንም። ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ በይፋ ውድቅ የተደረጉትን የቀድሞ ጉዳዮችን መልሶ ለማምጣት ሙከራ እያደረጉ ነው። ስለሆነም፣ በድንጋጌዎቹ ላይ ምንም ለውጥ እንዳለመኖሩ በኢትዮጵያ በኩል ጥንቃቄ የተሞላበት አካሄድ ያስፈልጋል።”
ግብፅ የአፍሪካ ሕብረት አደራዳሪነትን በመተው ወደ አሜሪካ የምታደላው አድሎአዊ ድጋፍ እንደምታገኝ ስለምታውቅ ነው ያሉት አማካሪው፣ ለኢትዮጵያ ግድቡ የውኃ ቴክኒክ መሆኑን አጽናኦት ሰጥተዋል፡፡
"ለግብፅ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ የፖለቲካ አጀንዳ ሊሆን ይችላል፤ ለኢትዮጵያ ግን ውኃ የቴክኒክና የልማት ጉዳይ ነው። ማኅበረሰባችንን ከድህነት የምናወጣበት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል የምናመነጭበት እና የምግብ ዋስትናችንን የምናረጋግጥበት ስትራቴጂካዊ ሀብታችን ነው" ብለዋል።
አማካሪው አክለውም፣ ትራምፕ በመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው እ.ኤ.አ በ2020 የኢትዮጵያን ሉዓላዊ መብት የሚጋፋ እና ተቀባይነት የሌለው የውል ረቂቅ አዘጋጅተው እንደነበር አስታውሰው ኢትዮጵያ አሁንም ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባት አሳስበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X