ትራምፕ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ የኢትዮጵያን እና የግብፅን ድርድር ዳግም ለማስጀመር ቃል ገቡ
18:35 18.06.2026 (የተሻሻለ: 18:44 18.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ትራምፕ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ የኢትዮጵያን እና የግብፅን ድርድር ዳግም ለማስጀመር ቃል ገቡ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ውዝግብ በድጋሚ እንደሚመለከቱት የገለጹ ሲሆን፤ ፕሮጀክቱ “ለግብፅ ከፍተኛ ችግሮችን” እየፈጠረባት ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
በፈረንሳይ ኤቪያን ከተካሄደው የቡድን 7 ጉባኤ ጎን ለጎን ትራምፕ ከግብፅ አቻቸው አብደል ፈታህ ኤል-ሲሲ ጋር በነበራቸው የሁለትዮሽ ስብሰባ ላይ፣ የናይል (ዓባይ) ወንዝ ጉዳይ ከሚወያዩባቸው አጀንዳዎች መካከል አንዱ እንደደነበር ተናግረዋል፡፡
የውዝግቡ መንስኤ
ቀደም ሲል በግብፅ እና በኢትዮጵያ መካከል የነበረው መሠረታዊ አለመግባባት በግድቡ የውኃ ሙሌት ላይ የነበረ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት ግን በውኃው ፍሰት፣ አስተዳደር እና የውኃ ክፍፍል ስምምነት ላይ ሰፊ ልዩነቶችን ያካተተ ሆኗል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ እንደ ቅኝ ግዛት ውል የምታጣጥለው የ1952 የግብፅ እና ሱዳን የውኃ ክፍፍል ስምምነት ሌላኛው ያለመግባባታቸው ምክንያት ተደርጎ ይነሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X