የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በሀገር ውስጥ በኒውክሌር ሬአክተር ቴክኖሎጂ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠነውን ተማሪ ሊያስመርቅ ነው

© telegram sputnik_ethiopiaየአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በሀገር ውስጥ በኒውክሌር ሬአክተር ቴክኖሎጂ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠነውን ተማሪ ሊያስመርቅ ነው
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በሀገር ውስጥ በኒውክሌር ሬአክተር ቴክኖሎጂ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠነውን ተማሪ ሊያስመርቅ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.06.2026
ሰብስክራይብ

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በሀገር ውስጥ በኒውክሌር ሬአክተር ቴክኖሎጂ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠነውን ተማሪ ሊያስመርቅ ነው

በዩኒቨርሲቲው የኒውክሌር ሬአክተር ቴክኖሎጂ የልህቀት ማዕከል የድህረ-ምረቃ ተማሪ የሆነው ውባንተ ደሴ፣ ዘርፉ ላይ በማተኮር ያካሄደውን የማስተርስ ዲግሪ ማሟያ ጥናታዊ ጽሑፍ አጠናቆ በማቅረብ ተቀባይነት አግኝቷል።

በኒውክሌር ቁሶች ዘርፍ ያተኮረው ይህ ጥናት፣ የኒውክሌር ኃይል ሥርዓቶችን ደኅንነትና አስተማማኝነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በመግለጫው፣ ለውባንተ ብቻ ሳይሆን "ከፍተኛ ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎችን ለማፍራት እና በኒውክሌር ሳይንስና ኢንጂነሪንግ ዘርፍ ዘመናዊ ምርምሮችን ለማካሄድ ለተቋቋሙት ለአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ለኒውክሌር ሪአክተር ቴክኖሎጂ የልህቀት ማዕከል ትልቅ ስኬት ነው፡፡"  ብሏል፡፡

ይህ ውጤት ኢትዮጵያ በሳይንስና ከፍተኛ ቴክኖሎጂ ያላትን አቅም ለማሳደግና ተቋሙ የፈጠራ ማዕከል ለመሆን ለያዘው ግብ ትልቅ ማረጋገጫ መሆኑ ተመላክቷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0