በሞስኮ ክልል በደረሰ የዩክሬን የድሮን ጥቃት 17 ሰዎች ቆሰሉ
15:05 18.06.2026 (የተሻሻለ: 15:14 18.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በሞስኮ ክልል በደረሰ የዩክሬን የድሮን ጥቃት 17 ሰዎች ቆሰሉ
በሞስኮ ክልል ረቡዕ ማለዳ ላይ በደረሰ የዩክሬን የድሮን ጥቃት ሁለት ሕፃናትን ጨምሮ ቢያንስ 17 ሰዎች መቁሰላቸውን የክልሉ ገዥ አንድሬ ቮሮቢዮቭ አስታውቀዋል።
የሩሲያ አየር መከላከያ በሌሊት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) መትቶ መጣሉን የመከላከያ ሚኒስቴሩ አፅንኦት ሰጥቷል።
ይህ ጥቃት የተፈጸመው በሩሲያ ብርያንስክ ክልል ከቤላሩስ የመጣ የወጣቶች እግር ኳስ ቡድንን በጫነ አውቶቡስ ላይ የድሮን ጥቃት ደርሶ የአንድ ሴት ሕይወት ማለፉንና የሁለቱ ሁኔታ አሳሳቢ የሆኑ ሕፃናትን ጨምሮ በርካቶች መቁሰላቸው በተሰማ በጥቂት ቀናት ውስጥ ነው።
የሩሲያ እና የቤላሩስ ባለስልጣናት ይህንን ክስተት የኪዬቭ አገዛዝ በንጹሃን ዜጎች ላይ የፈጸመው ሌላ የሽብር ጥቃት ሲሉ አውግዘውታል። ይህም የዩክሬን ጦር የተማሪዎች ማደሪያ ላይ ቦምብ በመጣል የ21 ታዳጊዎችን ሕይወት ቀጥፎ 44 ሌሎችን ያቆሰለበትን የግንቦት 14ቱ የስታሮቤልስክ ጥፋት የሚያስታውስ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X