የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የመካከለኛው ምስራቅን ቀውስ ያረገበውን የአሜሪካ እና ኢራን የሰላም ስምምነት አደነቁ
14:40 18.06.2026 (የተሻሻለ: 14:44 18.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የመካከለኛው ምስራቅን ቀውስ ያረገበውን የአሜሪካ እና ኢራን የሰላም ስምምነት አደነቁ
የሕብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ፣ ስምምነቱ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ውጥረት ለመቀነስ እና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ትልቅ እርምጃ መሆኑን ገልጸው፣ ቀውሶችን በዲፕሎማሲ ለመፍታት አዲስ ተስፋ የፈነጠቀ ነው ብለዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስምምነቱ ግቡን እንዲመታ ላደረጉት አስተዋፅዖ እውቅና የሰጡ ሲሆን፣ የሁለቱ ወገኖች አመራሮች ላሳዩት ገንቢ ተሳትፎ ምስጋና አቅርበዋል።
በድርድሩ ሂደት ውስጥ ትልቅ እገዛ ላደረጉት ለፓኪስታን፣ ኦማን፣ ኳታር፣ ግብፅ እና ቱርክ የአደራዳሪነት ሚና ከፍተኛ አድናቆት ችሯል።
ሕብረቱ በውይይትና በዲፕሎማሲ የሚመጡ የሰላም አማራጮችን ሁሉ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ሊቀመንበሩ በድጋሚ አረጋግጠዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X