ከበልግ የሰብል ልማት ከ110 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚሰበሰብ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ
14:15 18.06.2026 (የተሻሻለ: 14:24 18.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ከበልግ የሰብል ልማት ከ110 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚሰበሰብ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ
በሚኒስቴሩ የሰብል ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ ተሾመ ገለቱ፣ በበልግ ወቅት 4.3 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ አፈጻጸሙ ከዕቅድ በላይ 102% መድረሱን ለአገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል።
ለዚህ ስኬታማ አፈጻጸም የዘንድሮው የበልግ ዝናብ ምቹ መሆንና የግብርና መካናይዜሽን መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ማበርከታቸው ተጠቅሷል፡፡ ከሰኔ ወር መጀመሪያ ጀምሮ ቀድመው የሚደርሱ የጥራጥሬና የቅባት ሰብሎችን የመሰብሰብ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ አጋጥሞ የነበረውን አነስተኛ የዝናብ እጥረትና በአንዳንድ አካባቢዎች የታየውን መጠነኛ የተባይ መከሰት በተሠሩ ፈጣን የመከላከል ሥራዎች ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር የተቻለ ሲሆን፥ በአሁኑ ወቅት በበልግ ምርት ላይ ምንም ዓይነት ሥጋት አለመኖሩ ተገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X