የአሜሪካ እና ኢራን የመግባቢያ ስምምነት የሆርሙዝ ሰርጥ በአስቸኳይ እንዲከፈት መንገድ ይጠርጋል - የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሻሪፍ

© telegram sputnik_ethiopiaየአሜሪካ እና ኢራን የመግባቢያ ስምምነት የሆርሙዝ ሰርጥ በአስቸኳይ እንዲከፈት መንገድ ይጠርጋል - የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሻሪፍ
የአሜሪካ እና ኢራን የመግባቢያ ስምምነት የሆርሙዝ ሰርጥ በአስቸኳይ እንዲከፈት መንገድ ይጠርጋል - የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሻሪፍ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.06.2026
ሰብስክራይብ

የአሜሪካ እና ኢራን የመግባቢያ ስምምነት የሆርሙዝ ሰርጥ በአስቸኳይ እንዲከፈት መንገድ ይጠርጋል - የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሻሪፍ

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት “ሁለቱም ወገኖች ለግጭቱ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ መፍትሔ ለመስጠት ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳያል” ሲሉ በሁለቱ ወገኖች መካከል በተደረገው ውይይት ዋና አገናኝ የነበሩት የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሻሪፍ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል።

ይህ የመግባቢያ ስምምነት ወዲያውኑ ሥራ ላይ እንደሚውል ያሰመሩበት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እንደ መጀመሪያ እርምጃ ኢራን “የሆርሙዝ ወሽመጥን በአስቸኳይ እንደምትከፍት እና አሜሪካም የጣለችውን የባሕር ኃይል እገዳ ወዲያውኑ እንደምታነሳ” ፅፈዋል።

የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶናልድ ትራምፕ “ለዲፕሎማሲ ላሳዩት ፅኑ ቁርጠኝነት” ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፣ የኢራንን አመራሮችም “የሰላምን ጥሪ በመቀበላቸው” አድንቀዋል። በተመሳሳይ ስምምነቱ እንዲሳካ እገዛ ላደረጉት ኳታር፣ ሳዑዲ ዓረቢያ፣ ቱርክ እና ግብፅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ለቀጣናው መረጋጋት እና “ለዚህ ስኬት መገኘት ያደረጉት ጥረት እጅግ ከፍተኛ ነበር” በማለት ለፓኪስታን ጦር አዛዥ ፊልድ ማርሻል አሲም ሙኒር ልዩ እውቅና ሰጥተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0