በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በአንድ ጊዜ 24 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ የኃይል መሙያ ጣቢያ ተመረቀ
12:15 18.06.2026 (የተሻሻለ: 12:24 18.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በአንድ ጊዜ 24 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ የኃይል መሙያ ጣቢያ ተመረቀ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር፥ ያስገነቡት ዘመናዊ የፈጣን ኃይል መሙያ ጣቢያ በቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ቅጥር ግቢ ውስጥ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
አገልግሎቱ በአዲስ አበባ ኮተቤ፣ ለቡ እና ፒያሳ ተመሳሳይ ጣቢያዎችን መክፈቱን አስታውሶ፥ በአሁኑ ወቅት በቢሾፍቱ፣ ሞጆ፣ ባቱ፣ አዳማ፣ ሻሸመኔ እና ሐዋሳ ከተሞች ተጨማሪ ጣቢያዎችን በመገንባት ላይ እንደሚገኝ ጠቁሟል።
በተጨማሪም 95 በመቶ የሀገሪቱን የገቢ-ወጪ ንግድ በሚያስተናግደው የኢትዮ-ጂቡቲ የትራንስፖርት ኮሪደር ላይ ደግሞ 16 አዳዲስ እጅግ ፈጣን የኃይል መሙያ ጣቢያዎችን ለመገንባት የዲዛይን ሥራዎችን እያጠናቀቀ መሆኑን ይፋ አድርጓል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X