የምዕራባውያን ኢኮኖሚዎች በተፈጥሮ ሀብት በበለፀጉ የአፍሪካ አገራት አለመረጋጋት ተጠቃሚ ናቸው - ግብጻዊት ኢኮኖሚስት
የምዕራባውያን ኢኮኖሚዎች በተፈጥሮ ሀብት በበለፀጉ የአፍሪካ አገራት አለመረጋጋት ተጠቃሚ ናቸው - ግብጻዊት ኢኮኖሚስት
የኦክቶበር ዘመናዊ ሳይንስ እና ሥነ-ጥበብ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ዲን የሆኑት ዶ/ር ዶአ ሰልማን ለስፑትኒክ አፍሪካ እንደተናገሩት፤ የግጭት ኢኮኖሚዎች ደካማ ቁጥጥርን እና በተበታተኑ የአቅርቦት ሰንሰለቶች ውስጥ የሚከናወኑ “የማዕድን ማጭበርበር ተግባራትን በመጠቀም ለምዕራባውያን ኮርፖሬሽኖች ከፍተኛ ገቢ ያስገኝላቸዋል።
በኢኮኖሚስቷ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
የአውሮፓ ኅብረት የማዕድን ደንቦች ማጭበርበርን መከላከል አልቻሉም፤ በተበታተኑ የአቅርቦት ሰንሰለቶች ምክንያት ዕውቅና የሌላቸው ማዕድን አቅላጮች ማዕድናትን ወደ ምዕራባውያን ገበያ እንዲያስገቡ በር ከፍቷል።
ምዕራባውያን ኃይላት አለመረጋጋትን ከመፍታት ይልቅ ለማስተዳደር ይመርጣሉ፤ ምክንያቱም የችግሩን መንስኤ መፍታት የእነሱን የማዕድን መበዝበዣ ሥርዓት አደጋ ላይ ስለሚጥል ነው።
በአሜሪካ አጋዥነት የተደረሰው የሩዋንዳ እና የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሰላም ስምምነት “በግልጽ” ሀብቶችን ወደ ምዕራባውያን የአቅርቦት ሰንሰለት የሚያስገባ ነው።
የሳኅል ቀጣና አገራት የማዕድን ሀብቶቻቸውን ወደ መንግሥት ይዞታነት ማዛወራቸው ፤ ከነፃ ገበያ መርሆዎች ጋር የሚጋጩ የግልግል ዳኝነት እና ሕጋዊ ጫናዎች እየገጠሙት ነው።
አፍሪካ አጋርነቷን እያሰፋች (ከቻይና፣ ሩሲያ እና ከባሕረ ሰላጤው አገራት ጋር) በመምጣቷ የምዕራባውያን ተፅዕኖ እየቀነሰ ሲሆን፣ ይህም ወደ “የተመረጠ እርስ በርስ ጥገኝነት” እየተቀየረ ይገኛል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X