በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል የጋራ የባዮሎጂ ምርምር ማዕከል መቋቋም ለሳይንሳዊ እድገትና ኢኮኖሚ ወሳኝ ነው - የዘርፉ ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopiaበኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል የጋራ የባዮሎጂ ምርምር ማዕከል መቋቋም ለሳይንሳዊ እድገትና ኢኮኖሚ ወሳኝ ነው - የዘርፉ ባለሙያ
በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል የጋራ የባዮሎጂ ምርምር ማዕከል መቋቋም ለሳይንሳዊ እድገትና ኢኮኖሚ ወሳኝ ነው - የዘርፉ ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.06.2026
ሰብስክራይብ

በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል የጋራ የባዮሎጂ ምርምር ማዕከል መቋቋም ለሳይንሳዊ እድገትና ኢኮኖሚ ወሳኝ ነው - የዘርፉ ባለሙያ

 

የባዮና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂዎች ማዕከል የጤና ባዮቴክኖሎጂ ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ሞላልኝ ቢተው ማዕከሉ ያዘጋጀውን እና ግንቦት 27፣ 2018 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀው በኢትዮጵያ መንግሥት እና በሩሲያ ፌዴሬሽን መካከል የጋራ የባዮሎጂ ምርምር ማዕከል ለማቋቋም የቀረበ ረቂቅ አዋጅ አስመልክቶ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ቆይታን አድርገዋል፡፡

ስምምነቱ በሀገሪቱ ያለውን የእውቀትና የከፍተኛ ላብራቶሪ መሠረተ-ልማት ክፍተት ለመሙላት ብሎም የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትላቸውን አዳዲስ ወረርሽኞች ለመከላከል ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር ዳይሬክተሩ አብራርተዋል።

"ከሩሲያ ጋር የሚኖረን የባዮሎጂካል ምርምር ተቋም መመስረት፣ አዳዲስ ግኝቶችን ለማግኘት እና ያልተጠቀምንበትን የብዝሃ ሀብት አቅም ወደ ኢኮኖሚ ለመቀየር እጅግ አስፈላጊ ነው። አብሮ መስራቱ ውዴታ ብቻ ሳይሆን ግዴታ ነው" ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በተለይም ምርምሩ በምግብ፣ በጤናና በግብርና ዘርፍ ራስን ለመቻል የሚደረገውን ጉዞ የሚያፋጥን በመሆኑ የሀገር ሉዓላዊነት ጉዳይ ነው ብለዋል።

"አሁን ላይ ባዮሎጂካል ጥናቶችን ማከናወን የሉዓላዊነት ጉዳይ ነው፡፡ የባዮሎጂካል ምርምር ማደጉ በምግብ ብቻ ሳይሆን በመድኃኒትና በሁሉም ነገር ራስን ለመቻል እንደ ሀገር የሉዓላዊነት ጉዳይ እየሆነ መጥቷል።"

ፎቶ፦ ሐምሌ 2015 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ እና የሩሲያ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ቫለሪ ፋልኮቭ ስምምነቱን ሲፈራረሙ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0