አገር በቀል የግብርና ዕውቀቶች ተገቢውን ዕውቅና አላገኙም - የኢትዮጵያ ዘላቂ የምግብ ሥርዓቶች እና አግሮ-ኢኮሎጂ ኮንሰርቲየም

ሰብስክራይብ

አገር በቀል የግብርና ዕውቀቶች ተገቢውን ዕውቅና አላገኙም - የኢትዮጵያ ዘላቂ የምግብ ሥርዓቶች እና አግሮ-ኢኮሎጂ ኮንሰርቲየም

የኮንሰርቲየሙ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ባዩሽ ፀጋዬ፣ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እኚህን ዕውቀቶች እና ልምዶች እንደ ዋነኛ መሣሪያ መጠቀም እንደሚገባ ዛሬ በተካሄደው የከፍተኛ ባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ላይ አሳስበዋል።

"ሆኖም የአየር ንብረት ለውጥ፣ የመሬት መራቆት፣ የአፈር ለምነት መቀነስ፣ የብዝሃ ሕይወት መመናመን እና የውኃ እጥረት በዘርፉ ላይ ከባድ ፈተና እየደቀኑ ከመሆኑም በላይ የማኅበረሰቡንና የሥነ-ምህዳሩን የአየር ንብረት የመቋቋም አቅም አደጋ ላይ እየጣሉት ነው።" ብለዋል።

ተጽዕኖዎቹን ለመቋቋም የኢትዮጵያ መንግሥት የምግብ ሥርዓትን ማሸጋገር የሚያስችል የረጅም ጊዜ ማዕቀፍ ሆኖ የሚያገለግል ብሔራዊ የአግሮ-ኢኮሎጂ ስትራቴጂ ማዘጋጀቱን መናገራቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።

የስፑትኒክ አፍሪካ ቪዲዮ ተጨማሪ መረጃዎችን ይዟል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0