የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ታሪካዊ ሰነዶችን ወደ ዲጂታል ሥርዓት ለማስገባት የሚያስችል የመረጃ ማዕከል አስመረቀ

ሰብስክራይብ

  የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ታሪካዊ ሰነዶችን ወደ ዲጂታል ሥርዓት ለማስገባት የሚያስችል የመረጃ ማዕከል አስመረቀ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ጋር በመተባበር፥ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ለማገዝ የተቋሙን ታሪካዊና ባህላዊ የመረጃ ሀብቶች ዲጂታይዝ የማድረግ ሥራ በይፋ አስጀምሯል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ፣ መሥሪያ ቤታቸው የሀገሪቱን የዕውቀት ማዕከላት በዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ለማገዝ እና ውድ ሀገራዊ ሰነዶችን የሚያስተዳድሩ ተቋማትን ዲጂታይዝ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የዲጂታላይዜሽን ሥራው ዕድሜ ጠገብ ብሔራዊ ሰነዶችንና ውድ የዕውቀት ሀብቶችን ከጥፋት ጠብቆ ለትውልድና ለተመራማሪዎች ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ታሪክን በቴክኖሎጂ አስደግፎ ማዘመን የኢትዮጵያን ባህላዊ ማንነት ለመጠበቅና ለቱሪዝም አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት መሆኑን ተመላክቷል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0