ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ እና ታንዛኒያ 50 ሚሊዮን አፍሪካውያንን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ያደረገው "ሚሽን 300" መርሃግብር ዋነኛ ተጠቃሚዎች መሆናቸው ተገለፀ
13:59 17.06.2026 (የተሻሻለ: 14:04 17.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ እና ታንዛኒያ 50 ሚሊዮን አፍሪካውያንን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ያደረገው "ሚሽን 300" መርሃግብር ዋነኛ ተጠቃሚዎች መሆናቸው ተገለፀ
ሦስቱ ሀገራት በዓለም ባንክ እና በአፍሪካ ልማት ባንክ ቡድኖች ጥምረት እ.ኤ.አ. በ2024 የተጀመረውና በ40 የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ከ50 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ያደረገው አኅጉር አቀፍ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት መርሃግብር ዋነኛ ተጠቃሚዎች ናቸው ተብሏል።
ይህ ስኬት እ.ኤ.አ. በ2030፣ ለ300 ሚሊዮን አፍሪካውያን የኤሌክትሪክ ኃይል ለማድረስ የተያዘውን ትልቅ ግብ ለማሳካት ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፦
በታንዛኒያ 7.5 ሚሊዮን፣
በኢትዮጵያ 4.6 ሚሊዮን እና
በናይጄሪያ 4.5 ሚሊዮን ሕዝብ አዲስ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ መሆን ችሏል።
በኢትዮጵያ በዋናነት የግሪድ መስመር ዝርጋታ ወጪን በቀነሱ እና ለአባወራዎችና ለንግድ ድርጅቶች አቅምን ያገናዘበ አቅርቦት በፈጠሩ ማሻሻያዎች ምክንያት 4.6 ሚሊዮን ሕዝብ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኗል ተብሏል።
ፕሮግራሙ እስካሁን ወደ 15 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የገንዘብ ድጋፍ ከዓለም ባንክና አፍሪካ ልማት ባንክ የተመደበለት ሲሆን የግል ባለሀብቶችንም በማሳተፍ ላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X