መንግሥት ህጻናት ላይ የተለየ ትኩረት አድርጎ እየሠራ ነው - የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር
16:55 16.06.2026 (የተሻሻለ: 17:18 16.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
መንግሥት ህጻናት ላይ የተለየ ትኩረት አድርጎ እየሠራ ነው - የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር
በየዓመቱ ሰኔ 9 ቀን የሚከበረው የአፍሪካ ህጻናት ቀን ለእያንዳንዱ አፍሪካዊ ህጻን ውኃ እና የንጽህና አጠባበቅ አቅርቦቶችን ማረጋገጥ በሚል መሪ ቃል ታስቦ ውሏል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት በሴቶችና ማኅበራዊ ሚኒስቴር አማካኝነት የሀገሪቱን ህጻናት ከመጠበቅ እና ከመንከባከብ አኳያ በዙ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ፤ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የህጻናት መብት ስርጸትና ስብዕና ቀረጻ ዴስክ ኃላፊ በለጠ ዳኘ ቀኑን አስመልክተው ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል፡፡
ኃላፊው ህጻናት ላይ ትኩረት አድርገው እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትንም ዘርዝረዋል፦
በተለያዩ ግንዛቤ ማስጨበጫ መንዶች የህጻናትን መብት ማስከበር፣
ለህጻናት ምቹና ተስማሚ አካባቢዎችን መፍጠር፣
ለችግር የተጋለጡ ህጻናት የሚደግፉበትን ሥርዓት መፍጠር፣
ህጻናትን የሚያሳትፉ እና ሃሳባቸውን መግለጽ የሚችሉባቸውን መድረኮች ማመቻቸት፣
የህጻናት ጥበቃ ስርዓትን ማጎልበት፣
ህጻናት ሀገራቸውን እንዲያውቁ ማድረግ፡፡
“አሁን በተለይ ለህጻናት የተለየ ትኩረት ተሰጥቶ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራቶች አሉ። ከህጻናት ምገባ ብንጀምር በአዲስ አበባ በሁሉም የመንግሥት ትምህርት ቤቶች የህጻናት ምገባ የተጀመረበት ሂደት አለ። ከኮሪደር ሥራዎች ጋር በተያያዘ ደግሞ አዲስ አበባን ጨምሮ ሌሎች ክልል ከተሞችም ላይ በሚከናወኑ ሥራዎች የህጻናት መዝናኛና መጫወቻዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ በስፋት እየተሠሩ ነው።”
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X