ኢትዮጵያ ወደ ቻይና የምትልካቸው ምርቶች የ67 በመቶ ዕድገት እንዳስመዘገቡ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ
15:35 16.06.2026 (የተሻሻለ: 15:44 16.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ወደ ቻይና የምትልካቸው ምርቶች የ67 በመቶ ዕድገት እንዳስመዘገቡ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ
ሀገሪቱ ባለፉት አምስት ዓመታት ወደ ቻይና ምርቶችን በመላክ 804.163 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታለች።
በተለይም እ.ኤ.አ በ2025 የበጀት ዓመት የተመዘገበው የ369.4 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ከ2024 ጋር ሲነጻጸር የ251 በመቶ ታሪካዊ ዕድገት አሳይቷል።
ይህ የውጭ ንግድ አፈጻጸም ከኢትዮጵያ አጠቃላይ የውጭ ንግድ የቻይናን የገበያ ድርሻ ወደ 4.4 በመቶ ያሳደገው ሲሆን ቡና እና ሰሊጥ ዋነኞቹ ተጠቃሽ ምርቶች ናቸው።
በሌላ በኩል፤ የሁለቱ ሀገራት አጠቃላይ የንግድ ልውውጥ ባለፉት አምስት ዓመታት 29.12 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል ሲል ሚኒስቴሩ ባጋራው መግለጫ አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X