የግብርና ሚኒስቴር በዓመት 63 ሚሊዮን እንቁላል የማሳቀፍ አቅም ያለው የዶሮ ጫጩት ማስፈልፈያ ለመገንባት ውል ተፈራረመ

© telegram sputnik_ethiopiaየግብርና ሚኒስቴር በዓመት 63 ሚሊዮን እንቁላል የማሳቀፍ አቅም ያለው የዶሮ ጫጩት ማስፈልፈያ ለመገንባት ውል ተፈራረመ
የግብርና ሚኒስቴር በዓመት 63 ሚሊዮን እንቁላል የማሳቀፍ አቅም ያለው የዶሮ ጫጩት ማስፈልፈያ ለመገንባት ውል ተፈራረመ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.06.2026
ሰብስክራይብ

የግብርና ሚኒስቴር በዓመት 63 ሚሊዮን እንቁላል የማሳቀፍ አቅም ያለው የዶሮ ጫጩት ማስፈልፈያ ለመገንባት ውል ተፈራረመ

ፕሮጀክቱ ከአፍሪካ ልማት ባንክ በተገኘ 10.15 ሚሊዮን ዶላር ብድር እንደሚገነባ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

 

ውሉን በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ እና የአግሪፋም ኩባንያ ተወካይ ጃሪ ዣኦ የተፈራረሙ ሲሆን ግንባታው ከአንድ ሳምንት በኋላ እንደሚጀመር እና በ12 ወራት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ እንደታቀደ ተገልጿል።

ስምምነቱ ኢትዮጵያ የግብርና ዘርፏን ለማዘመን፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና ቀልጣፋና ገበያ ተኮር የእንስሳት ሀብት ሥርዓት ለመገንባት ከምታደርጋቸው ሰፊ ጥረቶች መካከል አንዱ ነው ተብሏል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0