ኢትዮጵያ የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ የፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት ከሩሲያ ተጨማሪ ማዳበሪያ ለመግዛት ጥያቄ ካቀረቡ ሀገራት መካከል አንዷ ናት - የግብርና ሚኒስቴር

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ የፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት ከሩሲያ ተጨማሪ ማዳበሪያ ለመግዛት ጥያቄ ካቀረቡ ሀገራት መካከል አንዷ ናት - የግብርና ሚኒስቴር

 

በሆርሙዝ ወሽመጥ ዙሪያ የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ በርካታ የውጭ አጋሮቻችን የናይትሮጅን እና ፎስፈረስ ማዳበሪያ አቅርቦት እንዲጨምርላቸው ጠይቀዋል ሲሉ የሩሲያ የግብርና ሚኒስትር ኦክሳና ሉት ለሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።

ዋና ዋና ዝርዝሮች፦

በቀጣናዊ ግጭቶች ተፅዕኖ ስር ስላለወደቀ፤ የፖታሽ ማዳበሪያ አቅርቦት የተረጋጋ ነው።

ኢትዮጵያ ከፍተኛ መጠን ማዳበሪያ እንዲቀርብላት በተለየ ሩሲያን ጠይቃለች።

ሞስኮ አስተማማኝ አቅርቦት ለማረጋገጥ አጋሮቿ ወደመካከለኛ ጊዜ ውሎች፤ በተለይም ወደ ሦስት ዓመት ስምምነቶች እንዲሸጋገሩ ጠይቃለች።

የሩሲያ አምራቾች ለትብብር ዝግጁ መሆናቸውን የገለፁት ሚኒስትሯ፤ ሀገሪቱ እያደገ የመጣውን ፍላጎት መሠረት በማድረግ ቁልፍ የውጭ አጋሮቿን ጥያቄ ማሟላት እንደምትችል እምነታቸውን ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0