ግብፅ በኒውክሌር ኢነርጂ ዘርፍ ከሩሲያ ጋር ያላትን ትብብር ለማስቀጠል እንደምትፈልግ ሚኒስትሩ ገለጹ

© telegram sputnik_ethiopiaግብፅ በኒውክሌር ኢነርጂ ዘርፍ ከሩሲያ ጋር ያላትን ትብብር ለማስቀጠል እንደምትፈልግ ሚኒስትሩ ገለጹ
ግብፅ በኒውክሌር ኢነርጂ ዘርፍ ከሩሲያ ጋር ያላትን ትብብር ለማስቀጠል እንደምትፈልግ ሚኒስትሩ ገለጹ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.06.2026
ሰብስክራይብ

ግብፅ በኒውክሌር ኢነርጂ ዘርፍ ከሩሲያ ጋር ያላትን ትብብር ለማስቀጠል እንደምትፈልግ ሚኒስትሩ ገለጹ

የኤል-ዳባ የኒውክሌር ጣቢያ ግንባታ በዕቅዱ መሠረት እየሄደ መሆኑን፤ የሀገሪቱ የኤሌክትሪክ እና ታዳሽ ኢነርጂ ሚኒስትር ማህሙድ ኢስማት ለስፑትኒክ የዜና ወኪል ተናግረዋል።

ግብፅ ከዚህ ቀደም በሩሲያ አነስተኛና ሞዱላር የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎች ላይ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት መግለጿ ይታወሳል።

በአፍሪካ የመጀመሪያው የሮሳቶም ፕሮጀክት፤ የኤል-ዳባ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ፤ ከካይሮ በስተሰሜን ምዕራብ 350 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ በሚገኘው የግብፅ ማትሩህ ግዛት ውስጥ ይገነባል። ጣቢያው አራት በሩሲያ የሚገነቡ ቪቪኢአር-1200 የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎችን ያካትታል። በአጠቃላይ 4.8 ጊጋ ዋት የሚጠጋ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ይኖራቸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0