ጋና እና ኮትዲቯር የኮኮዋ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠናከር መግባባት ላይ ደረሱ

ሰብስክራይብ

ጋና እና ኮትዲቯር የኮኮዋ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠናከር መግባባት ላይ ደረሱ

 

ሁለቱ ሀገራት የዘርፉን አቅም እና የአርሶ አደሮች ትርፋማነት ለማሳደግ ትብብራቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ በማቅረብ፤ የጋራ የኮኮዋ ጥምረታቸውን 7ኛ የአመራር ኮሚቴ ስብሰባ በአቢጃን ከፍተዋል።

 

የኮትዲቯር የግብርና ሚኒስትር ብሩኖ ናባኜ ኮኔ፤ አርሶ አደሮች ተገቢውን ገቢ እንዲያገኙ ለማረጋገጥ የተጣጣመ/ወጥ የሆነ የዋጋ አሰጣጥ እንደሚያስፈልግ አጽንዖት ሰጥተዋል።

 

"ዋጋን በማጣጣም ተገቢውን ገቢ እና ፍትሕን ማረጋገጥ ወሳኝ ጉዳይ ነው። ኮኮዋ ከምንም በላይ ለአርሶ አደሮች የተሻለ የኑሮ ደረጃ ዋስትና መስጠት አለበት" ሲሉ ተናግረዋል።

 

ተነሳሽነቱ የሁለትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር፣ የኑሮ ደረጃን ለማሻሻል እና ይበልጥ ዘላቂ ለሆነ የኮኮዋ ምርት ተጨባጭ ምክረ ሀሳቦችን ለማዘጋጀት ያለመ ነው።

 

"በዓለም ቀዳሚ የኮኮዋ አምራች የሆኑ ሁለት ሀገራት እንደመሆናችን መጠን፤ ኢኮኖሚያችንን ለመጠበቅ በተከታታይ እና ስልታዊ በሆነ መንገድ መንቀሳቀስ አለብን" ያሉት የጋና የገንዘብ ሚኒስትር ካሲየል አቶ ፎርሰን፤ ይህ አቀራረብ ሁለቱ ሀገራት መስተጓጎሎች ሲፈጠሩ ዝም ብሎ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ፤ ተግዳሮቶችን አስቀድመው እንዲገምቱ፣ ድንገተኛ አደጋዎችን እንዲያቃልሉ እና የዘርፉን የወደፊት ዕጣ ፈንታ እንዲቀርጹ እንደሚረዳቸው ገልጸዋል።

 

ከማኅበራዊ የትስስር ገፅ የተገኘ ቪዲዮ

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0