የኢትዮጵያ ምርጫ የሚዳኛው በኢትዮጵያውያን እንጂ በምዕራባውያን ሚዲያዎች እና ጋዜጠኞች አይደለም - የፖለቲካ እና ሕግ ምሁር

© telegram sputnik_ethiopiaየኢትዮጵያ ምርጫ የሚዳኛው በኢትዮጵያውያን እንጂ በምዕራባውያን ሚዲያዎች እና ጋዜጠኞች አይደለም - የፖለቲካ እና ሕግ ምሁር
የኢትዮጵያ ምርጫ የሚዳኛው በኢትዮጵያውያን እንጂ በምዕራባውያን ሚዲያዎች እና ጋዜጠኞች አይደለም - የፖለቲካ እና ሕግ ምሁር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.06.2026
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ምርጫ የሚዳኛው በኢትዮጵያውያን እንጂ በምዕራባውያን ሚዲያዎች እና ጋዜጠኞች አይደለም - የፖለቲካ እና ሕግ ምሁር

ግንቦት 24፣ 2018 ዓ.ም የተካሄደው 7ኛው ብሔራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነጻ እና ፍትሐዊ እንደነበር የተናገሩት ፕሮፈሰር አለማየሁ ገብረማርያም፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ የመጨረሻ ውሳኔውን ሰጥቷል ብለዋል።

"ዋናው ነጥብ ይህ ነው፤ ኢትዮጵያውያን ሌሎች፣ ኒው ዮርክ ታይምስ ወይም ቢቢሲ አልያም የአሜሪካ መንግሥት ወይም ሌላ ማንኛውም አካል ምርጫውን በተመለከተ ስለሚሰጡት አስተያየት ምንም አይጨንካቸውም። የኢትዮጵያ ምርጫ የሚዳኘው በኢትዮጵያ ሕዝብ ነው።"

ምዕራባውያን ሚዲያዎች፣ ጋዜጠኞች እንዲሁም ተንታኝ እና ጦማሪ ነን የሚሉቱ፤ ከውጭ ሆነው የምርጫውን ውጤት ዋጋ ማሳጣት እንደማይችሉ ያነሱት ፕሮፌሰሩ፤ ችግር ካለም በኢትዮጵያ ፍርድ ቤት፣ ሕግ እና ሕገ-መንግሥት መሠረት እንደሚፈታ ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

"እኛ ዲሞክራሲያችንን የምንመራው በራሳችን፣ በኢትዮጵያዊ መንገድ ነው። የኢትዮጵያዊ የዲሞክራሲ መንገድ 'መደመር' ይባላል። የመደመር ዲሞክራሲ ሕዝቡ በምርጫ ሂደት ውስጥ አንድ ላይ በመሰባሰብ፣ ድምፁን በመስጠት እንዲሁም የወደፊት ሕይወቱንና ዕጣ ፈንታውን በመወሰን የሚፈጥረው ውህደት ማለት ነው።"

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0