- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

የተዘረፉ ቅርሶች፡- የአፍሪካን የታሪክ እውነት ለማስመለስ የሚደረገው ዓለም አቀፍ ትግል

የተዘረፉ ቅርሶች፡- የአፍሪካን የታሪክ እውነት ለማስመለስ የሚደረገው ዓለም አቀፍ ትግል
ሰብስክራይብ
“[…] ከአፍሪካ በጉልበት የተወሰዱ የተለያዩ ቅርሶች ለአፍሪካውያን ባለቤቶቻቸው ሳይመለሱ በአውሮፓ ሙዚየሞች እንዲቆዩ የሚደረገው ደህንነታቸው በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲጠበቅ ነው የሚለው መከራከሪያ እውነታነት የለውም። ምክንያቱም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በአውሮፓ ውስጥ የሚገኙ ብዙ ሙዚየሞች በጦር መሳሪያውች ተደብድበዋልና። በቅርቡ በፈረንሳዩ ሉቭር ሙዚየም ጭምር በርካታ ስርቆቶች ተፈጽመዋል። ስለዚህ በምዕራቡ አገራት ያሉ ሙዚየሞች በሙሉ አስተማማኝ ናቸው ማለት አይቻልም” ሲሉ የማህበራዊ ጉዳዮች ተመራማሪው አሉላ ፓንከረስት (ፒኤችዲ) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በቀዳሚ ጉዳዩ፣ የአፍሪካን የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ትክክለኛ መኖሪያቸው ለመመለስ የሚደረገውን ታሪካዊ፣ ስልታዊ እና ጥልቅ ስሜት የሚንጸባረቅበትን አፍሪካዊ እንቅስቃሴ ያስቃኘናል። ለዚህም የማህበራዊ ጉዳዮች ተመራማሪውን አሉላ ፓንከረስት (ፒኤችዲ) አነጋግረናል። እ.ኤ.አ. ሰኔ 11 እና 12 ቀን 2026 በአዲስ አበባ የተካሄደው አንደኛው ዓለም አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ እና የቴክኖሎጂ ውድድር ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የምንቃኝበት ሁለታኛው ጉዳያችን ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ደግሞ ሐሳባቸዉን ሊያጋሩን ብሩክ ከድር (ፒኤችዲ) የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፣ አናንድ አንባላጋን (ፒኤችዲ) የቴክኒክና ሙያ (TVET) የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ተባባሪ ፕሮፌሰር እና ፋራይ ቺጋሩ (ፒኤችዲ)፤ ከማላዊ የመጡ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ አነጋግረናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripods Pocket CastsPodcast AddictCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0