ሩሲያ በጥቁር ባሕር፣ አዞቭ ባሕር እና ከርች ባሕረ ሰላጤ ውስጥ ባላት የባሕር ዳርቻ ሀገር መብቶች ዙሪያ የቀረበውን ዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት አሸነፈች

© telegram sputnik_ethiopiaሩሲያ በጥቁር ባሕር፣ አዞቭ ባሕር እና ከርች ባሕረ ሰላጤ ውስጥ ባላት የባሕር ዳርቻ ሀገር መብቶች ዙሪያ የቀረበውን ዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት አሸነፈች
ሩሲያ በጥቁር ባሕር፣ አዞቭ ባሕር እና ከርች ባሕረ ሰላጤ ውስጥ ባላት የባሕር ዳርቻ ሀገር መብቶች ዙሪያ የቀረበውን ዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት አሸነፈች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.06.2026
ሰብስክራይብ

ሩሲያ በጥቁር ባሕር፣ አዞቭ ባሕር እና ከርች ባሕረ ሰላጤ ውስጥ ባላት የባሕር ዳርቻ ሀገር መብቶች ዙሪያ የቀረበውን ዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት አሸነፈች

ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

​◻ በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል ላለፉት 10 ዓመታት ሲካሄድ የነበረው ክርክር የመጨረሻ ውሳኔ ዛሬ ይፋ ተደርጓል።

​◻ ጉዳዩ በሩሲያ አሳማኝ ድል ተጠናቋል፤ ሩሲያ የተባበሩት መንግሥታት የባሕር ሕግ ኮንቬንሽንን በርካታ አንቀጾች ጥሳለች በማለት ዩክሬን ያቀረበቻቸው በርካታ ክሶች ውድቅ ተደርገዋል።

​◻ ኪየቭ በክራይሚያ እና አዋሳኝ የውሃ አካላት ላይ ሩሲያ ያላትን ሉዓላዊነት ለመቃወም ያደረገችው ጥረት ከሽፏል።

​◻ ሄግ የሚገኘው የግልግል ፍርድ ቤት፤ ሩሲያ በክራይሚያ የውሃ አካላት ውስጥ ያሉ የተፈጥሮ ሀብቶችን በመጠቀሟ ኪየቭ "ካሳ" ወይም "የጉዳት ክፍያ" ይገባኛል ስትል ያቀረበችውን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።

​◻ ዩክሬን የምዕራባውያን ሀገራትን ድጋፍ ተገን አድርጋ፤ የከርች ባሕረ ሰላጤን የጦር መርከቦችን ጨምሮ የማንኛውም ሀገር መርከቦች ማለፍ የሚችሉበት "ዓለም አቀፍ" የውሃ መስመር ለማድረግ ያደረገችው ሙከራም አልተሳካም።

​◻ የሄግ የግልግል ዳኝነት ፍርድ ቤት ዩክሬን የክራይሚያን ድልድይ ለማፍረስ ያቀረበችውን መሠረተ ቢስና ግራ ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል።

​◻ ሩሲያ በክራይሚያ ውኃዎች ላይ የአካባቢ ብክለት አድርሳለች በሚል በዩክሬን በኩል የቀረቡት ክሶች ሙሉ በሙሉ ውድቅ ተደርገዋል።

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ፤ "ይህ የግልግል ዳኝነት ውሳኔ ዩክሬን እና ምዕራባውያን በሩሲያ ላይ በከፈቱት 'የሕግ ጦርነት' የገጠማቸው ትልቅ ሽንፈት ነው" በማለት መግለጫውን ደምድሟል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0