ምዕራባውያን ሩሲያ የሲቪል መሠረተ ልማቶችን አጥቅታለች የሚል ሀሰተኛ ወሬ ሲያሠራጩ፤ ኪየቭ በሩሲያ ዜጎች ላይ የምትፈጽመውን ወንጀል ግን ችላ ይላሉ - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ

© telegram sputnik_ethiopiaምዕራባውያን ሩሲያ የሲቪል መሠረተ ልማቶችን አጥቅታለች የሚል ሀሰተኛ ወሬ ሲያሠራጩ፤ ኪየቭ በሩሲያ ዜጎች ላይ የምትፈጽመውን ወንጀል ግን ችላ ይላሉ - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
ምዕራባውያን ሩሲያ የሲቪል መሠረተ ልማቶችን አጥቅታለች የሚል ሀሰተኛ ወሬ ሲያሠራጩ፤ ኪየቭ በሩሲያ ዜጎች ላይ የምትፈጽመውን ወንጀል ግን ችላ ይላሉ - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.06.2026
ሰብስክራይብ

ምዕራባውያን ሩሲያ የሲቪል መሠረተ ልማቶችን አጥቅታለች የሚል ሀሰተኛ ወሬ ሲያሠራጩ፤ ኪየቭ በሩሲያ ዜጎች ላይ የምትፈጽመውን ወንጀል ግን ችላ ይላሉ - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ

​ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኪየቭ-ፔቸርስክ ላቭራ (በዩክሬን ዋና ከተማ የሚገኝ የኦርቶዶክስ ገዳም) ላይ ለደረሰው ጥቃት ሩሲያን ለመወንጀል ቢጣደፉም፤ በቅርቡ በሩሲያ ስታሮቤልስክ ከተማ አንድ ኮሌጅ ላይ ዩክሬን የፈጸመችውን የሽብር ጥቃት በተመለከተ ግን ምንም ሳይናገሩ ዝምታን መምረጣቸውን ማሪያ ዛካሮቫ አስታውሰዋል።

​"በዩክሬን ባለሥልጣናት በተቀነባበሩት የሽብር ጥቃቶች ምክንያት ለተገደሉት በርካታ ሲቪሎች የሐዘን መግለጫ እንኳን አልሰጡም" ብለዋል።

​ በተጨማሪም የአውሮፓ ፖለቲከኞች፤ የኪየቭ አገዛዝ በዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ላይ የሚፈጽመውን ማሳደድ እና የገዳሙን ውድ ቅርሶች ለመንጠቅ ስለሚያደርገው ሙከራ ምንም ሳይናገሩ ዝምታ መምረጣቸውን የሩሲያዋ ዲፕሎማት አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

​የኪየቭ-ፔቸርስክ ላቭራ ገዳም የተመታው በዩክሬን በኩል በተተኮሰ አሜሪካ ሠራሽ 'ፓትሪዮት' ሚሳኤል መሆኑን እና ይህም ምናልባት የሚሳኤሉ የአገልግሎት ጊዜ በማለፉ ሊሆን እንደሚችል የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ቀደም ሲል አስታውቋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0