የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በያዝነው ክረምት በሰሜንና ሰሜን ምሥራቅ አካባቢዎች የሚጥለው ዝናብ አስቀድሞ ሊቋረጥ እንደሚችል አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopiaየኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በያዝነው ክረምት በሰሜንና ሰሜን ምሥራቅ አካባቢዎች የሚጥለው ዝናብ አስቀድሞ ሊቋረጥ እንደሚችል አስታወቀ
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በያዝነው ክረምት በሰሜንና ሰሜን ምሥራቅ አካባቢዎች የሚጥለው ዝናብ አስቀድሞ ሊቋረጥ እንደሚችል አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.06.2026
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በያዝነው ክረምት በሰሜንና ሰሜን ምሥራቅ አካባቢዎች የሚጥለው ዝናብ አስቀድሞ ሊቋረጥ እንደሚችል አስታወቀ

የክረምቱ ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ ቢጀምርም፤ በሰሜንና ሰሜን ምሥራቅ አካባቢዎች ቀድሞ ሊያቆም ስለሚችል የግብርና የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎች መከናወን እንዳለባቸው ኢንስቲትዩቱ ጠቁሟል።

በሌላ በኩል መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ለሚያገኙ የምዕራብ አጋማሽ አካባቢዎች ከባድ ዝናብ ሰብል እንዳያበላሽ፤ በእርሻ ማሳዎች ውስጥ የውኃ ማፋሰሻ ቦዮችን ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግ የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አሳምነው ተሾመ አሳስበዋል ሲል የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

የትንበያ ማስረጃዎች ከነሐሴ ወር ጀምሮ የኤልኒኖ ክስተት አይሎ እንደሚቀጥል ያሳያሉ ሲሉም ኃላፊው ጨምረው ገልጸዋል።

በፓስፊክ ውቅያኖስ ሙቀት መጨመር ምክንያት በዘንድሮ ክረምት ኤልኒኖ መከሰት መቻሉ 80% መድረሱን የዓለም ሜትሮሎጂ ድርጅት ቀደም ሲል አስታውቋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0