ኢትዮጵያ በዓለም ሁለተኛዋ ትልቅ የቡና አምራች ሀገር ለመሆን ጥረቷን አጠናክራለች - የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን
18:01 15.06.2026 (የተሻሻለ: 18:04 15.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በዓለም ሁለተኛዋ ትልቅ የቡና አምራች ሀገር ለመሆን ጥረቷን አጠናክራለች - የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን
ባለሥልጣኑ የቡና ምርትን ሜካናይዝድ ለማድረግ፣ ምርታማነትን ለመጨመር እና ኢንዱስትሪውን ለማዘመን ከምርምር ተቋማት ጋር እየሠራ እንደሚገኝ የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታጋይ ኑሩ ለመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል።
የምርት ግቡን ለማሳካት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት፦
◻ የቆዩ የቡና ዛፎችን ለመተካት ድርቅና በሽታን የሚቋቋሙ 47 አዳዲስ ዝርያዎች ማዘጋጀት፣
◻ ወደ ሚካናይዝድ ግብርና መሸጋገር፣
◻ ለቡና አምራቾች የተለያዩ ማበረታቻዎችን ማመቻቸት።
ኃላፊው ባለሃብቶች የኢትዮጵያን የቡና ዘርፍ ለመለወጥ በሚደረገው ጥረት ከመንግሥት ጋር እንዲተባበሩም ጥሪ አቅርበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X