ናሚቢያ ራቅ ባሉ አካባቢዎች የኢንተርኔት አገልግሎትን ለማጠናከር የአንጎላውን "አንጎሳት-2" ሳተላይት ለመጠቀም ወሰነች
17:01 15.06.2026 (የተሻሻለ: 17:04 15.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ናሚቢያ ራቅ ባሉ አካባቢዎች የኢንተርኔት አገልግሎትን ለማጠናከር የአንጎላውን "አንጎሳት-2" ሳተላይት ለመጠቀም ወሰነች
የናሚቢያ ቴሌኮም የመሬት የመገናኛ መሠረተ ልማት ውስን በሆነባቸው አካባቢዎች የአንጎላን "አንጎሳት-2" ሳተላይት በመጠቀም፤ ኢንተርኔትና ዳታ ለማድረስ ከአንጎላ የጠፈር ኤጀንሲ ጋር የሙከራ የንግድ ስምምነት መፈራረሙን አስታውቋል።
ስምምነቱ ይፋ የሆነው የሁለቱ ሀገራት የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትሮች በተገኙበት የሉአንዳው የ "አንጎቲክ 2026" ፎረም ላይ ነው።
የናሚቢያ ቴሌኮም ፕሬዝዳንት ፊማኔኬኒ ፔትሩስ፤ “በዚህ የሙከራ የንግድ ስምምነት አማካኝነት ቴክኖሎጂን ብቻ እየፈተሽን አይደለም፤ የቀጣናችንን የዲጂታል ትስስር የወደፊት ዕጣ ፈንታ በተግባር እየቀረጽን ነው” ብለዋል።
ሙከራው ያስፈለገው የኢንተርኔት አገልግሎቱ በሰፊው ጥቅም ላይ ከመዋሉ በፊት የቴክኒክ ብቃቱንና የንግድ አዋጭነቱን ለመገምገም እንደሆነ ፔትሩስ ገልጸዋል።
"አንጎሳት-2"፤ እ.ኤ.አ በ2022 በአንጎላ እና በሩሲያ የጋራ ጥረት ወደ ጠፈር የተላከ ከፍተኛ ዳታ የማስተላለፍ አቅም ያለው፤ መላውን አፍሪካ እና ከፊል አውሮፓን የሚሸፍን፤ ሳተላይት ነው። አንጎላ እ.ኤ.አ ከ2023 ጀምሮ ሳተላይቱ ለደቡብ አፍሪካ የልማት ማኅበረሰብ አባል ሀገራት አገልግሎት እንዲሰጥ ፈቃድ ሰጥታለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X