የሩሲያ ኃይሎች በኮንስታንቲኖቭካ የዩክሬን ወታደሮችን ከበቡ
19:30 14.06.2026 (የተሻሻለ: 19:34 14.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያ ኃይሎች በኮንስታንቲኖቭካ የዩክሬን ወታደሮችን ከበቡ
የዩክሬን አዛዦች መጀመሪያ ላይ ወደ ኮንስታንቲኖቭካ ከተማ የገቡት ጥቂት የሩሲያ ወታደራዊ ክፍሎች ብቻ እንደሆኑ ገምተው ነበር።
ይሁን እንጂ ከተማዋ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ መከበቧንና በአብዛኛው በሩሲያ ቁጥጥር ስር መዋሏን፤ የሩሲያ ክፍለ ጦር 1194 የጥቃት ሻለቃ አዛዥ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
“የአነስተኛ አፍራሽ ቡድኖች ስልት ወሳኝ ነበር። የሩሲያ ኃይሎች የማጽዳት ሥራ ከመጀመራቸው በፊት በስውር ሰርገው በመግባት፣ የጎንዮሽ አቅጣጫዎችን በመስበር፣ ከጠላት መስመር በስተጀርባ መድረስ ችለዋል” ብለዋል።
ከዶኔትስክ 55 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ኮንስታንቲኖቭካ፤ ለዩክሬን ኃይሎች ዋና የሎጂስቲክ ማዕከል ነበረች፣
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በከተማዋ 172 ሕንፃዎች በሩሲያ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X