ቢያንስ 20 የአፍሪካ እና የእስያ የወሊድ ባለሙያዎች በፖርቱጋል ለሚካሄደው ዓለም አቀፍ ኮንግረስ ቪዛ ተከለከሉ

© telegram sputnik_ethiopiaቢያንስ 20 የአፍሪካ እና የእስያ የወሊድ ባለሙያዎች በፖርቱጋል ለሚካሄደው ዓለም አቀፍ ኮንግረስ ቪዛ ተከለከሉ
ቢያንስ 20 የአፍሪካ እና የእስያ የወሊድ ባለሙያዎች በፖርቱጋል ለሚካሄደው ዓለም አቀፍ ኮንግረስ ቪዛ ተከለከሉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.06.2026
ሰብስክራይብ

ቢያንስ 20 የአፍሪካ እና የእስያ የወሊድ ባለሙያዎች በፖርቱጋል ለሚካሄደው ዓለም አቀፍ ኮንግረስ ቪዛ ተከለከሉ

በዓለም አቀፉ የአዋላጅ ነርሶች ኮንፌዴሬሽን ኮንግረስ ላይ እንዳይሳተፉ ከተከለከሉት መካከል የኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ፣ ሩዋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ኡጋንዳ፣ ሴራሊዮን፣ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ፣ ባንግላዲሽ እና ሕንድ የወሊድ ባለሙያዎች እንደሚገኙበት መገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል።

“በየሁለት ደቂቃው አንዲት እናት በወሊድ ምክንያት ትሞታለች። ይህ የቪዛ ክልከላ ድምፃቸው ይበልጥ ሊሰማ የሚገባቸውን ባለሙያዎች የሚያፍን ነው” ሲሉ የማህፀንና የወሊድ ባለሙያዎች ኮንፌዴሬሽን አማካሪ ኬት ስትሪንገር ተናግረዋል።

“ከበለጸጉ” ሀገራት የመጡ ልዑካን በሙሉ እንዲገቡ መፈቀዱን በመጥቀስ፤ ሁኔታውን ከእግር ኳስ ዳኛው ኡመር አርታን ክስተት ጋር በማነጻጸር “የቅኝ ግዛት አድልዎ” መገለጫ ነው ሲሉ ኮንነውታል።

ዓለም አቀፉ የወሊድ ባለሙያዎች ኮንግረስ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ የሚከሰተውን የ260 ሺህ እናቶች ሞት እንዲሁም በተወለዱ በመጀመሪያው ወር ውስጥ የሚሞቱ 4.2 ሚሊዮን ጨቅላ ህጻናትን ቁጥር ለመቀነስ ያለመ የውይይት መድረክ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0