ለ2018/19 የምርት ዘመን ከ23 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ እንደሚቀርብ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopiaለ2018/19 የምርት ዘመን ከ23 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ እንደሚቀርብ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ
ለ2018/19 የምርት ዘመን ከ23 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ እንደሚቀርብ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.06.2026
ሰብስክራይብ

ለ2018/19 የምርት ዘመን ከ23 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ እንደሚቀርብ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ

 

በዘንድሮ የምርት ዘመን የማዳበሪያም ሆነ የምርጥ ዘር ግብዓት አቅርቦት እጥረት እንዳልነበር እና በአሁኑ ሰዓት ግብዓቱ ለአርሶ አደሩ በየክልሎች እየተሠራጨ መሆኑን በሚኒስቴሩ የሰብል ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ ተሾመ ገለቱ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ገልጸዋል።

 

ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በዘንድሮው የመኸር እርሻ ከ22.36 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት መታቀዱንም አክለዋል።

 

የግብርና ሚኒስቴር በዘንድሮው ዓመት "አንድም ለእርሻ የሚሆን መሬት ጦም ማደር የለበትም" የሚል ግብ አንግቦ እየሠራ እንደሚገኝም አመላክተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0