የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ለጀግናዋ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ የረዳት ኮሚሽነርነት ማዕረግ ሰጠ
17:22 14.06.2026 (የተሻሻለ: 17:24 14.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ለጀግናዋ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ የረዳት ኮሚሽነርነት ማዕረግ ሰጠ
የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የስፖርት ክለብ እና የሙዚቃና ቴዓትር ቡድን 40ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓሉን በትናንትናው ዕለት ባከበረበት ወቅት የማዕረግ ሽልማቱን ለአትሌቷ ማበርከቱን በማኅበራዊ የትስስር ገፁ አጋርቷል።
ለአትሌት ጥሩነሽ የተሰጠው ዕውቅና የተቋሙ ከፍተኛ ማዕረግ ነው።
ኮማንደር ጥሩነሽ ዲባባ ከ15 በላይ የወርቅ ሜዳልያዎችን ያሸነፈች አትሌት ስትሆን፤ በአራት የኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ በመሳተፍ 3 የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ እና አንድ ነሀስ ያሸነፈች ታላቅ ኢትዮጵያዊ አትሌት ነች።
በመርኃ-ግብሩ ላይ ከአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በተጨማሪ በስፖርት ክለቡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱት አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ ፋጡማ ሮባ፣ ስለሽ ስህን፣ ሰለሞን ባረጋ እንዲሁም ለሌሎች አንጋፋ ስፖርተኞች ዕውቅና ተሰጥቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia