የሩሲያ ሳይንቲስቶች ውጤታማ የሆኑ የትንኝ መከላከያዎችን ለመፈተሽ ወደ ሳኀል ቀጠና ተጓዙ

ሰብስክራይብ

የሩሲያ ሳይንቲስቶች ውጤታማ የሆኑ የትንኝ መከላከያዎችን ለመፈተሽ ወደ ሳኀል ቀጠና ተጓዙ

​ሳኅል ለምን ተመረጠ?

የጥናቱ መሪና የሩሲያ ተመራማሪ ሮማን ያኮቭሌቭ እንደተናገሩት፤ "የመከላከያ መሳሪያዎቹን ትክክለኛ ውጤታማነት ለማረጋገጥ፤ ትንኞች እጅግ በጣም ኃይለኛ ወደሆኑበት እና በሺዎች የሚቆጠሩበት ትንኞች ወዳሉበት የወባ በሽታ ዋና መናኸሪያ ማዕከል ድረስ ተጉዘናል" ብለዋል።

ምርመራው የተካሄደበት ቦታ፦

​የጥናት ቡድኑ የትንኝ ማባረሪያ እና መከላከያዎችን ባማኮ አቅራቢያ በሚገኘው "ሴቤኒኮሮ" እና በማሊ የኒጀር ወንዝ ተፋሰስ ውስጥ የፈተሸ ሲሆን በእነዚህ ቦታዎች አደገኛ የሆኑት "የኤዴስ"፣ "አኖፌልስ" እና "ኩሌክስ" የትንኝ ዝርያዎች ዓመቱን ሙሉ በንቃት ይንቀሳቀሳሉ።

​ ምልከታዎቹ የተካሄዱት ትንኞች በብዛት በሚንቀሳቀሱባቸው ሰዓታት ነው። ይኸውም በከተማ አካባቢዎች ከምሽቱ 2፡00 እስከ 4፡00 ሰዓት እንዲሁም ከመኖሪያ መንደሮች ራቅ ባሉ ስፍራዎች ደግሞ ከምሽቱ 5፡00 እስከ ሌሊቱ 7፡00 ሰዓት ድረስ።

ውጤቶች፦

እጅግ ውጤታማ፦ የኤሌክትሪክ ማሞቂያ መሳሪያዎች እጅግ ውጤታማ ሆነው ተገኝተዋል። እንደ ተመራማሪዎቹ ገለጻ፤ እነዚህ መሳሪያዎች በዙሪያቸው የማይታይ የመከላከያ "ጉልላት" የሚፈጥሩ ሲሆን በዚህ ክልል ውስጥ የሚገቡ ትንኞች ጥቃት የሚያደርሱበትን አካል የመለየት አቅማቸውን ያጣሉ አሊያም እየበረሩ ይረግፋሉ።

አነስተኛ ውጤት ያሳዩ፦ የሚጨሱ የትንኝ ጥቅል ክሮች፣ ጠረን ያላቸው ሻማዎች እና የአልትራሶኒክ መሳሪያዎች እጅግ ዝቅተኛ የሆነ ውጤት አሳይተዋል።

ጥናቱ የተካሄደው በቲዩመን ስቴት ዩኒቨርሲቲና ቶምስክ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ሳይንቲስቶች እና በማሊ፣ ጊኒ፣ ሀንጋሪ፣ ጀርመን፣ ግሪክ፣ ካናዳ፣ ሊቱዌኒያ እና አሜሪካ አቻዎቻቸው ትብብር ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0