የሶፍ ዑመር ዋሻ ዘመናዊ የመብራት መሠረተ ልማት ዝርጋታ ተጠናቀቀ

© telegram sputnik_ethiopiaየሶፍ ዑመር ዋሻ ዘመናዊ የመብራት መሠረተ ልማት ዝርጋታ ተጠናቀቀ
የሶፍ ዑመር ዋሻ ዘመናዊ የመብራት መሠረተ ልማት ዝርጋታ ተጠናቀቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.06.2026
ሰብስክራይብ

የሶፍ ዑመር ዋሻ ዘመናዊ የመብራት መሠረተ ልማት ዝርጋታ ተጠናቀቀ

የምህንድስና ባለሙያዎች በቀላሉ ሊጎዳ የሚችለውን የምድር ውስጥ የተፈጥሮ አካባቢ ለመጠበቅ ሲባል አሃዛዊ (ዲጂታል) የዲዛይን ማዕቀፍ ጥቅም ላይ አውለዋል።

የፕሮጀክቱ ዋና ዋና ክንውኖች፦

አስተዳደር እና የቦታው ታሪካዊነት፦ በኦሮሚያ ክልል የሚገኘውና በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት የዓለም ቅርስ እጩ የሆነውን የ15.1 ኪሎ ሜትር የኖራ ድንጋይ ስብስብ የቱሪዝም ማሻሻያ ፕሮጀክት የመራው የቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ነው። ቦታው በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ታሪካዊ ስፍራ ያለው ሲሆን በዋሻው ውስጥ የሚገኙት የድንጋይ ቅርጾች በ100 ብር ኖት ጀርባ ላይ ታትመው ይገኛሉ።

 

ጥንቃቄ የተሞላበት ተከላ፦ በጥንታዊ የጂኦሎጂካል ቅርፆች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከል ሠራተኞች ከባድ ማሽነሪዎችን ከመጠቀም በመቆጠብ ተከላውን ያከናወኑት የእጅ መሳሪያዎችን ብቻ በመጠቀም ነው።

 

የብርሃን እና የውሃ ትዕይንት፦ የተገጠመው ሥርዓት ዘመናዊ እና ተፈጥሯዊ ብርሃንን የተላበሰ የዋሻ መስህብን የሚፈጥር ሲሆን ተለዋዋጭ ብርሃንን በመጠቀም የውሃ እና የመብራት ቅንጅታዊ ትዕይንትን ያቀርባል።

ተጨማሪ ግንባታዎች፦ ፕሮጀክቱ በዋሻው ውስጥ የተለየ የመሬት ገጽታ አዳራሽን እና ምቹ የመሰብሰቢያ ቦታዎችን መገንባትንም ያካትታል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
የሶፍ ዑመር ዋሻ ዘመናዊ የመብራት መሠረተ ልማት ዝርጋታ ተጠናቀቀ - Sputnik አፍሪካ
1/3
© telegram sputnik_ethiopia
የሶፍ ዑመር ዋሻ ዘመናዊ የመብራት መሠረተ ልማት ዝርጋታ ተጠናቀቀ - Sputnik አፍሪካ
2/3
© telegram sputnik_ethiopia
የሶፍ ዑመር ዋሻ ዘመናዊ የመብራት መሠረተ ልማት ዝርጋታ ተጠናቀቀ - Sputnik አፍሪካ
3/3
1/3
2/3
3/3
አዳዲስ ዜናዎች
0