የሶማሊላንድን ውዝግብ ለመፍታት ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ አማራጮችን አጢነናል - የሶማሊያ ፕሬዚዳንት
08:00 14.06.2026 (የተሻሻለ: 08:04 14.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሶማሊላንድን ውዝግብ ለመፍታት ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ አማራጮችን አጢነናል - የሶማሊያ ፕሬዚዳንት
በሶማሊያ ፌደራል መንግሥት እና ራሷን ሪፐብሊክ ብላ ባወጀችው ሶማሊላንድ መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ለመፍታት፤ መንግሥታቸው በመጨረሻም ውይይት እና ማሳመንን ምርጫው እንዳደረገ ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ ለሀገር ውስጥ የዜና ምንጭ ገልጸዋል።
እስራኤል እ.አ.አ ከ1991 ጀምሮ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሀገራት እውቅና ሳታገኝ ለቆየችው ሶማሊላንድ፤ በታህሳስ ወር ይፋዊ እውቅና ሰጥታለች።
ኢትዮጵያ የባሕር ዳርቻ እና የባሕር ኃይል ጦር ሠፈር ለማግኘት በ2024 ከሶማሊላንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርማለች። አዲስ አበባ እና ሞቃዲሾ በቱርክ አሸማጋይነት ልዩነቶቻቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X