“እንደ ሩሲያ ካለች ታላቅ ሀገር ጋር በመቆም እኛም ታላቅ እንሆናለን” - የማሊ ባለሥልጣን

ሰብስክራይብ

“እንደ ሩሲያ ካለች ታላቅ ሀገር ጋር በመቆም እኛም ታላቅ እንሆናለን” - የማሊ ባለሥልጣን

ማሊ እና ሩሲያ "በምዕራባውያን ሀገራት የተስፋፋውን" ሽብርተኝነት በጋራ እየታገሉ መሆናቸውን የማሊ የደኅንነት ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ፉሴኑ ኦዋታራ በሩሲያ ብሔራዊ ቀን ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

በርካታ የማሊ ጠቅላይ ሚኒስትሮች እና ባለሙያዎች በሩሲያ የተማሩ በመሆናቸው በሁለቱ ሀገራት ዲያስፖራዎች መካከል ጠንካራ ትስስር እንዳለም አክለዋል።

የማሊ ባህር ማዶ የሚኖሩ ዜጎች ጉዳይ ሚኒስትር ሞሳ አግ አታሄር በበኩላቸው፤ ሩሲያ “ከማሊ ስትራቴጂካዊ አጋሮች መካከል ወሳኝ ቦታ ተቆናጣለች” ብለዋል።

አታሄር በሩሲያ ኤምባሲ በተዘጋጀው የሩሲያ ቀን ሥነ-ሥርዓት ላይ ያነሷቸው ሌሎች አንኳር ነጥቦች፦

ሁለቱም ሀገራት በሉዓላዊነት፣ በነጻነት እና መሠረታዊ ጥቅሞችን በማስከበር ረገድ ተመሳሳይ እሴቶችን ይጋራሉ።

አስሚ ጎይታ እ.ኤ.አ በ2025 በሞስኮ ያደረጉት ጉብኝት በንግድ፣ በቴክኖሎጂ እና በኢነርጂ ዘርፎች ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ አጠናክሮታል።

የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ የሞስኮ እና አፍሪካ የውይይት እና የምክክር መድረክ ነው።

ሩሲያ በምዕራብ አፍሪካ ያለውን አለመረጋጋት ለመፍታት ሥልጠና፣ የትጥቅ አቅርቦት እና የልምድ ልውውጥን ጨምሮ የማሊን ወታደራዊ አቅም ለማጠናከር ድጋፍ ትሠጣለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0